አል-ዐንከቡት · 41/69
ትርጉም ፊደሎች — ሱረቱ አል-ዐንከቡት
مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ ۝٤١
Masalul lazeenat takhazoo min doonil laahi awliyaaa`a kamasalil `ankaboot, ittakhazat baitaa; wa inna awhanal buyooti la baitul `ankaboot; law kaanoo ya`lamoon
📖 በአማርኛ
የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር)፡፡

🎧 ስሙ


📜 አንቀጽ 39-43 — ሱረቱ አል-ዐንከቡት

39وَقَارُونَ وَفِرْعَوْنَ وَهَامَانَ ۖ وَلَقَدْ جَاءَهُم مُّوسَىٰ بِالْبَيِّنَاتِ فَاسْتَكْبَرُوا فِي الْأَرْضِ وَمَا كَانُوا سَابِقِينَ
ቃሩንንም ፈርዖንንም ሃማንንም (አጠፋን)፡፡ ሙሳም በተዓምራቶች በእርግጥ መጣባቸው፡፡ በምድርም ላይ ኮሩ፡፡ አምላጪዎችም አልነበሩም፡፡
40فَكُلًّا أَخَذْنَا بِذَنبِهِ ۖ فَمِنْهُم مَّنْ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِ حَاصِبًا وَمِنْهُم مَّنْ أَخَذَتْهُ الصَّيْحَةُ وَمِنْهُم مَّنْ خَسَفْنَا بِهِ الْأَرْضَ وَمِنْهُم مَّنْ أَغْرَقْنَا ۚ وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيَظْلِمَهُمْ وَلَٰكِن كَانُوا أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
ሁሉንም በኅጢኣቱ ያዝነው፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፋስን የላክንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አልለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ያሰጠምንው አልለ፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡
41مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ
የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር)፡፡
42إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِ مِن شَيْءٍ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
አላህ ያንን ከእርሱ ሌላ የሚግገዙትን ማንኛውንም ያውቃል፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
43وَتِلْكَ الْأَمْثَالُ نَضْرِبُهَا لِلنَّاسِ ۖ وَمَا يَعْقِلُهَا إِلَّا الْعَالِمُونَ
እነዚህንም ምሳሌዎች ለሰዎች እንገልጻቸዋለን፡፡ ከሊቃውንቶቹም በስተቀር ሌሎቹ አያውቋትም፡፡
አል-ዐንከቡትቁርአን ማውጫ
69አንቀጽ
MeccanRevelation
41አንቀጽ

ትርጉም — አል-ዐንከቡት 41

ሱረቱ አል-ዐንከቡት አንቀጽ 41 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ…

ሱረቱ አንቀጽ 41/69 — ሱረቱ አል-ዐንከቡት العنكبوت (Meccan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ሱረቱ አል-ዐንከቡት ስሙ, ሱረቱ አል-ዐንከቡት ትርጉም, ሱረቱ አል-ዐንከቡት mp3, ሱረቱ አል-ዐንከቡት pdf. አንቀጽ 39–43. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Monday, September 7, 2026

Don't forget us in your sincere prayers