ሱረቱ አል-መዓሪጅ ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አል-መዓሪጅን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (44 አንቀጽ — مكية). አል-መዓሪጅ ስሙ, አል-መዓሪጅ ትርጉም, አል-መዓሪጅ mp3, አል-መዓሪጅ pdf.

ሱረቱ አል-መዓሪጅን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
سَأَلَ سَائِلٌ بِعَذَابٍ وَاقِعٍ ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡
لِّلْكَافِرِينَ لَيْسَ لَهُ دَافِعٌ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡
مِّنَ اللَّهِ ذِي الْمَعَارِجِ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡
تَعْرُجُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡
فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡
إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡
وَنَرَاهُ قَرِيبًا ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡
يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاءُ كَالْمُهْلِ ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡
وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡
وَلَا يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيمًا ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡
يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡
وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِ ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
በሚስቱም በወንድሙም፡፡
وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْوِيهِ ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡
وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنجِيهِ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡
كَلَّا ۖ إِنَّهَا لَظَىٰ ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡
نَزَّاعَةً لِّلشَّوَىٰ ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡
تَدْعُو مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّىٰ ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡
وَجَمَعَ فَأَوْعَىٰ ۝١٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 18
ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡
۞ إِنَّ الْإِنسَانَ خُلِقَ هَلُوعًا ۝١٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 19
ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡
إِذَا مَسَّهُ الشَّرُّ جَزُوعًا ۝٢٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 20
ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡
وَإِذَا مَسَّهُ الْخَيْرُ مَنُوعًا ۝٢١
📖 ትርጉም አንቀጽ 21
መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡
إِلَّا الْمُصَلِّينَ ۝٢٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 22
ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡
الَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَائِمُونَ ۝٢٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 23
እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡
وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَّعْلُومٌ ۝٢٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 24
እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡
لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ ۝٢٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 25
ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡
وَالَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ ۝٢٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 26
እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡
وَالَّذِينَ هُم مِّنْ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشْفِقُونَ ۝٢٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 27
እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡
إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْمُونٍ ۝٢٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 28
የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡
وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ ۝٢٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 29
እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ ۝٣٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 30
በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡
فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ ۝٣١
📖 ትርጉም አንቀጽ 31
ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡
وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ ۝٣٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 32
እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
وَالَّذِينَ هُم بِشَهَادَاتِهِمْ قَائِمُونَ ۝٣٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 33
እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡
وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ ۝٣٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 34
እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡
أُولَٰئِكَ فِي جَنَّاتٍ مُّكْرَمُونَ ۝٣٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 35
እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡
فَمَالِ الَّذِينَ كَفَرُوا قِبَلَكَ مُهْطِعِينَ ۝٣٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 36
ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?
عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ عِزِينَ ۝٣٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 37
ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡
أَيَطْمَعُ كُلُّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُدْخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٍ ۝٣٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 38
ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?
كَلَّا ۖ إِنَّا خَلَقْنَاهُم مِّمَّا يَعْلَمُونَ ۝٣٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 39
ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡
فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ ۝٤٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 40
በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
عَلَىٰ أَن نُّبَدِّلَ خَيْرًا مِّنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ ۝٤١
📖 ትርጉም አንቀጽ 41
ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا وَيَلْعَبُوا حَتَّىٰ يُلَاقُوا يَوْمَهُمُ الَّذِي يُوعَدُونَ ۝٤٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 42
ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡
يَوْمَ يَخْرُجُونَ مِنَ الْأَجْدَاثِ سِرَاعًا كَأَنَّهُمْ إِلَىٰ نُصُبٍ يُوفِضُونَ ۝٤٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 43
ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡
خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ۚ ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الَّذِي كَانُوا يُوعَدُونَ ۝٤٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 44
ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡
← 69 አል-መዓሪጅ (70/114) 71 →
ማንበብ ሱረቱ አል-መዓሪጅ አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

70المعارج Al-Ma'arij 📚 44 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አል-መዓሪጅ — 44 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers