ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (25 አንቀጽ — مكية). አል-ኢንሺቃቅ ስሙ, አል-ኢንሺቃቅ ትርጉም, አል-ኢንሺቃቅ mp3, አል-ኢንሺቃቅ pdf.

ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
إِذَا السَّمَاءُ انشَقَّتْ ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤
وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
وَإِذَا الْأَرْضُ مُدَّتْ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
وَأَلْقَتْ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتْ ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤
وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡
يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدْحًا فَمُلَاقِيهِ ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡
فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤
فَسَوْفَ يُحَاسَبُ حِسَابًا يَسِيرًا ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡
وَيَنقَلِبُ إِلَىٰ أَهْلِهِ مَسْرُورًا ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡
وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ وَرَاءَ ظَهْرِهِ ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤
فَسَوْفَ يَدْعُو ثُبُورًا ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡
وَيَصْلَىٰ سَعِيرًا ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡
إِنَّهُ كَانَ فِي أَهْلِهِ مَسْرُورًا ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡
إِنَّهُ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡
بَلَىٰ إِنَّ رَبَّهُ كَانَ بِهِ بَصِيرًا ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡
فَلَا أُقْسِمُ بِالشَّفَقِ ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡
وَاللَّيْلِ وَمَا وَسَقَ ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤
وَالْقَمَرِ إِذَا اتَّسَقَ ۝١٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 18
በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡
لَتَرْكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٍ ۝١٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 19
ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡
فَمَا لَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ ۝٢٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 20
የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?
وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ ۩ ۝٢١
📖 ትርጉም አንቀጽ 21
በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?)
بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا يُكَذِّبُونَ ۝٢٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 22
በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡
وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُوعُونَ ۝٢٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 23
አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡
فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ ۝٢٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 24
በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡
إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ أَجْرٌ غَيْرُ مَمْنُونٍ ۝٢٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 25
ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡
← 83 አል-ኢንሺቃቅ (84/114) 85 →
ማንበብ ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

84الإنشقاق Al-Inshiqaq 📚 25 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ — 25 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers