ሱረቱ አል-ዐለቅ ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አል-ዐለቅን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (19 አንቀጽ — مكية). አል-ዐለቅ ስሙ, አል-ዐለቅ ትርጉም, አል-ዐለቅ mp3, አል-ዐለቅ pdf.

ሱረቱ አል-ዐለቅን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
كَلَّا إِنَّ الْإِنسَانَ لَيَطْغَىٰ ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
أَن رَّآهُ اسْتَغْنَىٰ ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الرُّجْعَىٰ ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
أَرَأَيْتَ الَّذِي يَنْهَىٰ ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
عَبْدًا إِذَا صَلَّىٰ ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
أَرَأَيْتَ إِن كَانَ عَلَى الْهُدَىٰ ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
أَوْ أَمَرَ بِالتَّقْوَىٰ ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
أَرَأَيْتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
أَلَمْ يَعْلَم بِأَنَّ اللَّهَ يَرَىٰ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
كَلَّا لَئِن لَّمْ يَنتَهِ لَنَسْفَعًا بِالنَّاصِيَةِ ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
نَاصِيَةٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَةٍ ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
فَلْيَدْعُ نَادِيَهُ ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
ሸንጎውንም ይጥራ፡፡
سَنَدْعُ الزَّبَانِيَةَ ۝١٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 18
(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِب ۩ ۝١٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 19
ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡
← 95 አል-ዐለቅ (96/114) 97 →
ማንበብ ሱረቱ አል-ዐለቅ አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

96العلق Al-'Alaq 📚 19 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አል-ዐለቅ — 19 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers