PDF —
19 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ዐለቅ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ዐለቅ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ዐለቅ ትርጉም. ሱረቱ አል-ዐለቅ (Meccan) 19 አንቀጽ.

← አት-ቲንሱረቱ አል-ዐለቅ አል-ቀድር →


19 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﮕﮖﮗﮘﮙﮚ
96:1 አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
ﮛﮜﮝﮞﮟ
96:2 ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
ﮠﮡﮢﮣ
96:3 አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
ﮤﮥﮦﮧ
96:4 ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
ﮨﮩﮪﮫﮬﮭ
96:5 ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
ﮮﮯﮰﮱﯓ
96:6 በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
ﯔﯕﯖﯗ
96:7 ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
ﯘﯙﯚﯛﯜ
96:8 መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
ﯝﯞﯟﯠ
96:9 አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
ﯡﯢﯣﯤ
96:10 ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
ﯥﯦﯧﯨﯩﯪ
96:11 አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
ﯫﯬﯭﯮ
96:12 ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
ﭑﭒﭓﭔﭕ
96:13 አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
ﭖﭗﭘﭙﭚﭛ
96:14 አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
ﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
96:15 ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
ﭣﭤﭥﭦ
96:16 ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
ﭧﭨﭩ
96:17 ሸንጎውንም ይጥራ፡፡
ﭪﭫﭬ
96:18 (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
ﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳ
96:19 ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers