PDF —
19 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ኢንፊጣር pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ኢንፊጣር pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ኢንፊጣር ትርጉም. ሱረቱ አል-ኢንፊጣር (Meccan) 19 አንቀጽ.

← አት-ተክዊርሱረቱ አል-ኢንፊጣር አል-ሙጦፊፊን →


19 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭑﭒﭓﭔ
82:1 ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
ﭕﭖﭗﭘ
82:2 ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤
ﭙﭚﭛﭜ
82:3 ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤
ﭝﭞﭟﭠ
82:4 መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤
ﭡﭢﭣﭤﭥﭦ
82:5 ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡
ﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭ
82:6 አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
ﭮﭯﭰﭱﭲ
82:7 በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹ
82:8 በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡
ﭺﭻﭼﭽﭾ
82:9 ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡
ﭿﮀﮁﮂ
82:10 በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤
ﮃﮄﮅ
82:11 የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡
ﮆﮇﮈﮉ
82:12 የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡
ﮊﮋﮌﮍﮎ
82:13 እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡
ﮏﮐﮑﮒﮓ
82:14 ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡
ﮔﮕﮖﮗ
82:15 በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡
ﮘﮙﮚﮛﮜ
82:16 እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡
ﮝﮞﮟﮠﮡﮢ
82:17 የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
ﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩ
82:18 ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
ﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕ
82:19 (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers