ሱረቱ አት-ተክዊር ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አት-ተክዊርን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (29 አንቀጽ — مكية). አት-ተክዊር ስሙ, አት-ተክዊር ትርጉም, አት-ተክዊር mp3, አት-ተክዊር pdf.

ሱረቱ አት-ተክዊርን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤
وَإِذَا النُّجُومُ انكَدَرَتْ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤
وَإِذَا الْجِبَالُ سُيِّرَتْ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤
وَإِذَا الْعِشَارُ عُطِّلَتْ ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤
وَإِذَا الْوُحُوشُ حُشِرَتْ ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤
وَإِذَا الْبِحَارُ سُجِّرَتْ ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤
وَإِذَا النُّفُوسُ زُوِّجَتْ ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤
وَإِذَا الْمَوْءُودَةُ سُئِلَتْ ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤
بِأَيِّ ذَنبٍ قُتِلَتْ ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤
وَإِذَا الصُّحُفُ نُشِرَتْ ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤
وَإِذَا السَّمَاءُ كُشِطَتْ ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤
وَإِذَا الْجَحِيمُ سُعِّرَتْ ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤
وَإِذَا الْجَنَّةُ أُزْلِفَتْ ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤
عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّا أَحْضَرَتْ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤
فَلَا أُقْسِمُ بِالْخُنَّسِ ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡
الْجَوَارِ الْكُنَّسِ ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡
وَاللَّيْلِ إِذَا عَسْعَسَ ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤
وَالصُّبْحِ إِذَا تَنَفَّسَ ۝١٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 18
በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡
إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ ۝١٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 19
እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡
ذِي قُوَّةٍ عِندَ ذِي الْعَرْشِ مَكِينٍ ۝٢٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 20
የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡
مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ ۝٢١
📖 ትርጉም አንቀጽ 21
በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡
وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ ۝٢٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 22
ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡
وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ ۝٢٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 23
በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡
وَمَا هُوَ عَلَى الْغَيْبِ بِضَنِينٍ ۝٢٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 24
እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡
وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَيْطَانٍ رَّجِيمٍ ۝٢٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 25
እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡
فَأَيْنَ تَذْهَبُونَ ۝٢٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 26
ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ?
إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَالَمِينَ ۝٢٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 27
እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
لِمَن شَاءَ مِنكُمْ أَن يَسْتَقِيمَ ۝٢٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 28
ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡
وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ ۝٢٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 29
የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡
← 80 አት-ተክዊር (81/114) 82 →
ማንበብ ሱረቱ አት-ተክዊር አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

81التكوير At-Takwir 📚 29 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አት-ተክዊር — 29 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers