ሱረቱ አል-አዕላ ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አል-አዕላን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (19 አንቀጽ — مكية). አል-አዕላ ስሙ, አል-አዕላ ትርጉም, አል-አዕላ mp3, አል-አዕላ pdf.

ሱረቱ አል-አዕላን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡
الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡
وَالَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡
وَالَّذِي أَخْرَجَ الْمَرْعَىٰ ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡
فَجَعَلَهُ غُثَاءً أَحْوَىٰ ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡
سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡
إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡
وَنُيَسِّرُكَ لِلْيُسْرَىٰ ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡
فَذَكِّرْ إِن نَّفَعَتِ الذِّكْرَىٰ ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡
سَيَذَّكَّرُ مَن يَخْشَىٰ ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡
وَيَتَجَنَّبُهَا الْأَشْقَى ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
መናጢውም ይርቃታል፡፡
الَّذِي يَصْلَى النَّارَ الْكُبْرَىٰ ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡
ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡
قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡
وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡
بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡
وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡
إِنَّ هَٰذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ ۝١٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 18
ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡
صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ ۝١٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 19
በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡
← 86 አል-አዕላ (87/114) 88 →
ማንበብ ሱረቱ አል-አዕላ አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

87الأعلى Al-A'la 📚 19 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አል-አዕላ — 19 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers