PDF —
30 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ፈጅር pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ፈጅር pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ፈጅር ትርጉም. ሱረቱ አል-ፈጅር (Meccan) 30 አንቀጽ.

← አል-ጋሺያሱረቱ አል-ፈጅር አል-በለድ →


30 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭤﭥ
89:1 በጎህ እምላለሁ፡፡
ﭦﭧﭨ
89:2 በዐሥር ሌሊቶችም፡፡
ﭩﭪﭫ
89:3 በጥንዱም በነጠላውም፡፡
ﭬﭭﭮﭯ
89:4 በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡
ﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶ
89:5 በዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን?
ﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽ
89:6 ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን?
ﭾﭿﮀﮁ
89:7 በኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡
ﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈ
89:8 በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡
ﮉﮊﮋﮌﮍﮎ
89:9 በሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡
ﮏﮐﮑﮒ
89:10 በፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡
ﮓﮔﮕﮖﮗ
89:11 በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡
ﮘﮙﮚﮛ
89:12 በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን?)
ﮜﮝﮞﮟﮠﮡ
89:13 በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡
ﮢﮣﮤﮥ
89:14 ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡
ﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱ
89:15 ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡
ﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝ
89:16 በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡
ﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤ
89:17 ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡
ﯥﯦﯧﯨﯩﯪ
89:18 ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡
ﯫﯬﯭﯮﯯ
89:19 የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡
ﯰﯱﯲﯳﯴ
89:20 ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡
ﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼ
89:21 ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤
ﯽﯾﯿﰀﰁﰂ
89:22 መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ፤
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛ
89:23 ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ?
ﭜﭝﭞﭟﭠ
89:24 «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡
ﭡﭢﭣﭤﭥﭦ
89:25 በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡
ﭧﭨﭩﭪﭫ
89:26 የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡
ﭬﭭﭮﭯ
89:27 (ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ!
ﭰﭱﭲﭳﭴﭵ
89:28 «ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡
ﭶﭷﭸﭹ
89:29 «በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡
ﭺﭻﭼ
89:30 ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers