ሱረቱ አል-ጋሺያ ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አል-ጋሺያን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (26 አንቀጽ — مكية). አል-ጋሺያ ስሙ, አል-ጋሺያ ትርጉም, አል-ጋሺያ mp3, አል-ጋሺያ pdf.

ሱረቱ አል-ጋሺያን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْغَاشِيَةِ ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን?
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ خَاشِعَةٌ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡
عَامِلَةٌ نَّاصِبَةٌ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡
تَصْلَىٰ نَارًا حَامِيَةً ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡
تُسْقَىٰ مِنْ عَيْنٍ آنِيَةٍ ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡
لَّيْسَ لَهُمْ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٍ ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡
لَّا يُسْمِنُ وَلَا يُغْنِي مِن جُوعٍ ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاعِمَةٌ ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡
لِّسَعْيِهَا رَاضِيَةٌ ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡
فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡
لَّا تَسْمَعُ فِيهَا لَاغِيَةً ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡
فِيهَا عَيْنٌ جَارِيَةٌ ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡
فِيهَا سُرُرٌ مَّرْفُوعَةٌ ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡
وَأَكْوَابٌ مَّوْضُوعَةٌ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡
وَنَمَارِقُ مَصْفُوفَةٌ ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡
وَزَرَابِيُّ مَبْثُوثَةٌ ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡
أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
وَإِلَى السَّمَاءِ كَيْفَ رُفِعَتْ ۝١٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 18
ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!
وَإِلَى الْجِبَالِ كَيْفَ نُصِبَتْ ۝١٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 19
ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
وَإِلَى الْأَرْضِ كَيْفَ سُطِحَتْ ۝٢٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 20
ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)
فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ ۝٢١
📖 ትርጉም አንቀጽ 21
አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡
لَّسْتَ عَلَيْهِم بِمُصَيْطِرٍ ۝٢٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 22
በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡
إِلَّا مَن تَوَلَّىٰ وَكَفَرَ ۝٢٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 23
ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤
فَيُعَذِّبُهُ اللَّهُ الْعَذَابَ الْأَكْبَرَ ۝٢٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 24
አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
إِنَّ إِلَيْنَا إِيَابَهُمْ ۝٢٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 25
መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡
ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا حِسَابَهُم ۝٢٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 26
ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡
← 87 አል-ጋሺያ (88/114) 89 →
ማንበብ ሱረቱ አል-ጋሺያ አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

88الغاشية Al-Ghashiyah 📚 26 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አል-ጋሺያ — 26 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers