አል-አህቃፍ · 13/35
ትርጉም ፊደሎች — አል-አህቃፍ
إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ ۝١٣
Innal lazeena qaaloo Rabbunal laahu summas taqaamoo falaa khawfun `alaihim wa laahum yahzanoon
📖 በአማርኛ
እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ፣ ከዚያም ቀጥ ያሉ በነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነርሱም አያዝኑም፡፡
🎧 ስሙ

📜 አንቀጽ 11-15 — አል-አህቃፍ

11وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلَّذِينَ آمَنُوا لَوْ كَانَ خَيْرًا مَّا سَبَقُونَا إِلَيْهِ ۚ وَإِذْ لَمْ يَهْتَدُوا بِهِ فَسَيَقُولُونَ هَٰذَا إِفْكٌ قَدِيمٌ
እነዚያንም የካዱት ሰዎች ስለእነዚያ ስለ አመኑት ሰዎች (እምነቱ) «መልካም ነገር በኾነ ኖሮ ወደርሱ ባልቀደሙን ነበር» አሉ፡፡ በእርሱም ባልተመሩ ጊዜ «ይህ (ቁርኣን) ጥንታዊ ቅጥፈት ነው» ይላሉ፡፡
12وَمِن قَبْلِهِ كِتَابُ مُوسَىٰ إِمَامًا وَرَحْمَةً ۚ وَهَٰذَا كِتَابٌ مُّصَدِّقٌ لِّسَانًا عَرَبِيًّا لِّيُنذِرَ الَّذِينَ ظَلَمُوا وَبُشْرَىٰ لِلْمُحْسِنِينَ
ከበፊቱም የሙሳ መጽሐፍ መሪና ጸጋ ሲኾን አልለ፡፡ ይህም እነዚያን የበደሉትን ሊያስፈራራ በዐረብኛ ቋንቋ ሲኾን (የፊቶቹን መጻሕፍት) አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው፡፡ ለበጎ አድራጊዎችም ብስራት ነው፡፡
13إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ፣ ከዚያም ቀጥ ያሉ በነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነርሱም አያዝኑም፡፡
14أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ خَالِدِينَ فِيهَا جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው፡፡ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲኾኑ፡፡ በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ታላቅን ምንዳ (ይምመነዳሉ)፡፡
15وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ إِحْسَانًا ۖ حَمَلَتْهُ أُمُّهُ كُرْهًا وَوَضَعَتْهُ كُرْهًا ۖ وَحَمْلُهُ وَفِصَالُهُ ثَلَاثُونَ شَهْرًا ۚ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَبَلَغَ أَرْبَعِينَ سَنَةً قَالَ رَبِّ أَوْزِعْنِي أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ الَّتِي أَنْعَمْتَ عَلَيَّ وَعَلَىٰ وَالِدَيَّ وَأَنْ أَعْمَلَ صَالِحًا تَرْضَاهُ وَأَصْلِحْ لِي فِي ذُرِّيَّتِي ۖ إِنِّي تُبْتُ إِلَيْكَ وَإِنِّي مِنَ الْمُسْلِمِينَ
ሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ በችግር ላይ ኾና አረገዘችው፡፡ በችግርም ወለደችው፡፡ እርግዝናውና ከጡት መለያውም ሰላሳ ወር ነው፡፡ ጥንካሬውንም ወቅት በደረሰ ጊዜ (ከዚያ አልፎ) አርባ ዓመትንም በደረሰ ጊዜ «ጌታዬ ሆይ! ያችን በእኔ ላይና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም መልካም ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ፡፡ እኔ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም ከሙስሊሞ ነኝ» አለ፡፡
አል-አህቃፍቁርአን ማውጫ
35አንቀጽ
MeccanRevelation
13አንቀጽ

ትርጉም — አል-አህቃፍ 13

ሱረቱ አል-አህቃፍ አንቀጽ 13 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ፣ ከዚያም ቀጥ ያሉ በነርሱ ላይ…

ሱረቱ አንቀጽ 13/35 — አል-አህቃፍ الأحقاف (Meccan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: አል-አህቃፍ ስሙ, አል-አህቃፍ ትርጉም, አል-አህቃፍ mp3, አል-አህቃፍ pdf. አንቀጽ 11–15. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers