ሱረቱ አል-በለድ ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አል-በለድን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (20 አንቀጽ — مكية). አል-በለድ ስሙ, አል-በለድ ትርጉም, አል-በለድ mp3, አል-በለድ pdf.

ሱረቱ አል-በለድን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
لَا أُقْسِمُ بِهَٰذَا الْبَلَدِ ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡
وَأَنتَ حِلٌّ بِهَٰذَا الْبَلَدِ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡
وَوَالِدٍ وَمَا وَلَدَ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡
لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي كَبَدٍ ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
أَيَحْسَبُ أَن لَّن يَقْدِرَ عَلَيْهِ أَحَدٌ ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?
يَقُولُ أَهْلَكْتُ مَالًا لُّبَدًا ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡
أَيَحْسَبُ أَن لَّمْ يَرَهُ أَحَدٌ ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?
أَلَمْ نَجْعَل لَّهُ عَيْنَيْنِ ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?
وَلِسَانًا وَشَفَتَيْنِ ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡
وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?
فَلَا اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
فَكُّ رَقَبَةٍ ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡
أَوْ إِطْعَامٌ فِي يَوْمٍ ذِي مَسْغَبَةٍ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡
يَتِيمًا ذَا مَقْرَبَةٍ ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤
أَوْ مِسْكِينًا ذَا مَتْرَبَةٍ ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡
ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
(ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡
أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ ۝١٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 18
እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا هُمْ أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ ۝١٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 19
እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
عَلَيْهِمْ نَارٌ مُّؤْصَدَةٌ ۝٢٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 20
በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡
← 89 አል-በለድ (90/114) 91 →
ማንበብ ሱረቱ አል-በለድ አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

90البلد Al-Balad 📚 20 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አል-በለድ — 20 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers