ሱረቱ አሽ-ሸምስ ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አሽ-ሸምስን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (15 አንቀጽ — مكية). አሽ-ሸምስ ስሙ, አሽ-ሸምስ ትርጉም, አሽ-ሸምስ mp3, አሽ-ሸምስ pdf.

ሱረቱ አሽ-ሸምስን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡
وَالْقَمَرِ إِذَا تَلَاهَا ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤
وَالنَّهَارِ إِذَا جَلَّاهَا ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤
وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَاهَا ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤
وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤
وَالْأَرْضِ وَمَا طَحَاهَا ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
በምድሪቱም በዘረጋትም፤
وَنَفْسٍ وَمَا سَوَّاهَا ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
በነፍስም ባስተካከላትም፤
فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡
قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡
وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّاهَا ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡
كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِطَغْوَاهَا ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡
إِذِ انبَعَثَ أَشْقَاهَا ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡
فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ نَاقَةَ اللَّهِ وَسُقْيَاهَا ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡
فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمْدَمَ عَلَيْهِمْ رَبُّهُم بِذَنبِهِمْ فَسَوَّاهَا ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡
وَلَا يَخَافُ عُقْبَاهَا ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡
← 90 አሽ-ሸምስ (91/114) 92 →
ማንበብ ሱረቱ አሽ-ሸምስ አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

91الشمس Ash-Shams 📚 15 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አሽ-ሸምስ — 15 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers