PDF —
20 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-በለድ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-በለድ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-በለድ ትርጉም. ሱረቱ አል-በለድ (Meccan) 20 አንቀጽ.

← አል-ፈጅርሱረቱ አል-በለድ አሽ-ሸምስ →


20 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭽﭾﭿﮀﮁ
90:1 በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡
ﮂﮃﮄﮅﮆ
90:2 አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡
ﮇﮈﮉﮊ
90:3 በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡
ﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
90:4 ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗ
90:5 በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?
ﮘﮙﮚﮛﮜ
90:6 «ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡
ﮝﮞﮟﮠﮡﮢ
90:7 አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?
ﮣﮤﮥﮦﮧ
90:8 ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?
ﮨﮩﮪ
90:9 ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡
ﮫﮬﮭ
90:10 ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?
ﮮﮯﮰﮱ
90:11 ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡
ﯓﯔﯕﯖﯗ
90:12 ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
ﯘﯙﯚ
90:13 (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡
ﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡ
90:14 ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡
ﯢﯣﯤﯥ
90:15 የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤
ﯦﯧﯨﯩﯪ
90:16 ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡
ﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴ
90:17 (ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡
ﯵﯶﯷﯸ
90:18 እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗ
90:19 እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
ﭘﭙﭚﭛ
90:20 በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers