PDF —
49 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አት-ጡር pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አት-ጡር pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አት-ጡር ትርጉም. ሱረቱ አት-ጡር (Meccan) 49 አንቀጽ.



49 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﮞﮟ
52:1 በጡር (ጋራ) እምላለሁ፡፡
ﮠﮡﮢ
52:2 በተጻፈው መጽሐፍም፡፡
ﮣﮤﮥﮦ
52:3 በተዘረጋ ብራና ላይ፤ (በተጻፈው)፡፡
ﮧﮨﮩ
52:4 በደመቀው ቤትም፡፡
ﮪﮫﮬ
52:5 ከፍ በተደረገው ጣራም፡፡
ﮭﮮﮯ
52:6 በተመላው ባሕርም እምላለሁ፡፡
ﮰﮱﯓﯔﯕ
52:7 የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡
ﯖﯗﯘﯙﯚ
52:8 ለእርሱ ምንም ገፍታሪ የለውም፡፡
ﯛﯜﯝﯞﯟ
52:9 ሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይኾናል)፡፡
ﯠﯡﯢﯣ
52:10 ተራራዎችም መኼድን በሚኼዱበት (ቀን)፡፡
ﯤﯥﯦﯧ
52:11 ለአስተባባዮችም ያን ጊዜ ወዮላቸው፡፡
ﯨﯩﯪﯫﯬﯭ
52:12 ለእነዚያ እነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለኾኑት፡፡
ﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴ
52:13 ወደ ገሀነም እሳት በኀይል መግገፍተርን በሚግገፈተሩበት ቀን፡፡
ﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻ
52:14 ይህቺ ያቺ በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁት እሳት ናት፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗ
52:15 ይህ (ፊት ትሉ እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን?
ﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥ
52:16 ግቧት ታገሱም ወይም አትታገሡ በእናንተ ላይ እኩል ነው፡፡ የምትምመነዱት ትሠሩት የነበራችሁትን (ፍዳ) ብቻ ነው (ይባላሉ)፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪﭫ
52:17 አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው፡፡
ﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴ
52:18 ጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ኾነው (በገነት ውስጥ ናቸው)፡፡ የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው፡፡
ﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
52:19 «ትሠሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ኾናችሁ ብሉ፤ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄ
52:20 በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ኾነው (በገነት ይኖራሉ)፡፡ ዓይናማዎች በኾኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡
ﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙ
52:21 እነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በእምነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን በእነርሱ እናስጠጋለን፡፡ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፡፡ ሰው ሁሉ በሠራው ሥራ ተያዢ ነው፡፡
ﮚﮛﮜﮝﮞﮟ
52:22 ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን፡፡
ﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨ
52:23 በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፡፡ በውስጧ ውድቅ ንግግርና መውወንጀልም የለም፡፡
ﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱ
52:24 ለነርሱም የኾኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ (ለማሳለፍ) ይዘዋወራሉ፡፡
ﯓﯔﯕﯖﯗﯘ
52:25 የሚጠያየቁ ኾነውም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል፡፡
ﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠ
52:26 «እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ (ከቅጣት) ፈሪዎች ነበርን» ይላሉ፡፡
ﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧ
52:27 «አላህም በእኛ ላይ ለገሰ፡፡ የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን፡፡
ﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲ
52:28 «እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን፡፡ እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና» (ይላሉ)፡፡
ﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻ
52:29 (ሰዎችን) አስታውስም፡፡ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም ዕብድም አይደለህም፡፡
ﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃ
52:30 ይልቁንም የሞትን አደጋ በእርሱ የምንጠባበቅበት የኾነ ባለ ቅኔ ነው ይላሉን?
ﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊ
52:31 «ተጠባበቁ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚ
52:32 አእምሮዎቻቸው በዚህ ያዟቸዋልን? አይደለም በእውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናቸው፡፡
ﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
52:33 ወይም «ቀጠፈው ይላሉን?» አይደለም፤ በእውነቱ አያምኑም፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩ
52:34 እውነተኞችም ቢኾኑ መሰሉ የኾነን ንግግር ያምጡ፡፡
ﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
52:35 ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
52:36 ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃ
52:37 ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን?
ﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎ
52:38 ወይስ ለእነርሱ በእርሱ ላይ (ከሰማይ) የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? አድማጫቸውም (ሰማሁ ቢል) ግልጽን አስረጅ ያምጣ፡፡
ﮏﮐﮑﮒﮓﮔ
52:39 ወይስ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? ለእናንተም ወንዶች ልጆች አሏችሁን?
ﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜ
52:40 ወይስ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳው የተከበዱ ናቸውን?
ﮝﮞﮟﮠﮡﮢ
52:41 ወይስ ሩቁ ምስጢር እነርሱ ዘንድ ነውን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?
ﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫ
52:42 ወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያም የካዱት እነርሱ በተንኮል ተሸናፊዎች ናቸው፡፡
ﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗ
52:43 ወይስ ለእነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡
ﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡ
52:44 ከሰማይም ቁራጭን (በእነርሱ ላይ) ወዳቂ ኾኖ ቢያዩ ኖሮ «ይህ የተደራረበ ደመና ነው» ይሉ ነበር፡፡
ﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
52:45 ያንንም በእርሱ የሚግገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳ
52:46 ተንኮላቸው ከእነርሱ ምንንም የማይጠቅማቸውንና እነርሱም የማይርረዱበትን ቀን (እስከ ሚገናኙ ተዋቸው)፡፡
ﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾ
52:47 ለእነዚያ ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አልላቸው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡
ﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊ
52:48 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፡፡ ጌታህንም በምትነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው፡፡
ﰋﰌﰍﰎﰏﰐ
52:49 ከሌሊቱም አወድሰው፡፡ በከዋክብት መዳበቂያ ጊዜም (ንጋት ላይ አወድሰው)፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers