ሱረቱ አል-ሌል ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አል-ሌልን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (21 አንቀጽ — مكية). አል-ሌል ስሙ, አል-ሌል ትርጉም, አል-ሌል mp3, አል-ሌል pdf.

ሱረቱ አል-ሌልን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy
M Mahmoud Khalil Al-Husary
A Abdurrahman As-Sudais
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi
A Abdul Basit Abdul Samad
A Ali Al-Hudhaify
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy
A Abu Bakr Ash-Shaatree
M Muhammad Ayyoub
A Abdullah Basfar
A Abdullah Al-Juhani
M Maher Al Muaiqly
x1
وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَىٰ ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡
وَالنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡
وَمَا خَلَقَ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡
إِنَّ سَعْيَكُمْ لَشَتَّىٰ ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡
فَأَمَّا مَنْ أَعْطَىٰ وَاتَّقَىٰ ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡
وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤
فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْيُسْرَىٰ ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
وَأَمَّا مَن بَخِلَ وَاسْتَغْنَىٰ ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤
وَكَذَّبَ بِالْحُسْنَىٰ ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤
فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْعُسْرَىٰ ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
وَمَا يُغْنِي عَنْهُ مَالُهُ إِذَا تَرَدَّىٰ ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡
إِنَّ عَلَيْنَا لَلْهُدَىٰ ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡
وَإِنَّ لَنَا لَلْآخِرَةَ وَالْأُولَىٰ ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡
فَأَنذَرْتُكُمْ نَارًا تَلَظَّىٰ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡
لَا يَصْلَاهَا إِلَّا الْأَشْقَى ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡
الَّذِي كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡
وَسَيُجَنَّبُهَا الْأَتْقَى ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡
الَّذِي يُؤْتِي مَالَهُ يَتَزَكَّىٰ ۝١٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 18
ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡
وَمَا لِأَحَدٍ عِندَهُ مِن نِّعْمَةٍ تُجْزَىٰ ۝١٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 19
ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡
إِلَّا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِ الْأَعْلَىٰ ۝٢٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 20
ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡
وَلَسَوْفَ يَرْضَىٰ ۝٢١
📖 ትርጉም አንቀጽ 21
ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡
← 91 አል-ሌል (92/114) 93 →
ማንበብ ሱረቱ አል-ሌል አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

92الليل Al-Layl 📚 21 አንቀጽ مكية

ከቁጥር ወደ ቁጥር – ሱረቱ አል-ሌል — 21 አንቀጽ




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers