ሱረቱ አሽ-ሸምስ pdf — አውርድ (አማርኛ)
ሱረቱ አሽ-ሸምስ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አሽ-ሸምስ ትርጉም. ሱረቱ አሽ-ሸምስ (Meccan) 15 አንቀጽ.
Related
More ሱረቱ PDF
ሱረቱ አሽ-ሸምስ

ﭜﭝﭞ
91:1
በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡
ﭟﭠﭡﭢ
91:2
በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤
ﭣﭤﭥﭦ
91:3
በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤
ﭧﭨﭩﭪ
91:4
በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤
ﭫﭬﭭﭮ
91:5
በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤
ﭯﭰﭱﭲ
91:6
በምድሪቱም በዘረጋትም፤
ﭳﭴﭵﭶ
91:7
በነፍስም ባስተካከላትም፤
ﭷﭸﭹﭺ
91:8
አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡
ﭻﭼﭽﭾﭿ
91:9
(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡
ﮀﮁﮂﮃﮄ
91:10
(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡
ﮅﮆﮇﮈ
91:11
ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡
ﮉﮊﮋﮌ
91:12
ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡
ﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔ
91:13
ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡
ﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜ
91:14
አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡
ﮝﮞﮟﮠ
91:15
ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡
ቅዱስ ቁርኣን
Wednesday, September 9, 2026
Don't forget us in your sincere prayers







