አል-አህዛብ · 54/73
ትርጉም ፊደሎች — ሱረቱ አል-አህዛብ
إِن تُبْدُوا شَيْئًا أَوْ تُخْفُوهُ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا ۝٥٤
In tubdoo shai`an aw tukhfoohu fa innal laaha kaana bikulli shai`in `Aleemaa
📖 በአማርኛ
ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት (በርሱ ይመነዳችኋል)፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡

🎧 ስሙ


📜 አንቀጽ 52-56 — ሱረቱ አል-አህዛብ

52لَّا يَحِلُّ لَكَ النِّسَاءُ مِن بَعْدُ وَلَا أَن تَبَدَّلَ بِهِنَّ مِنْ أَزْوَاجٍ وَلَوْ أَعْجَبَكَ حُسْنُهُنَّ إِلَّا مَا مَلَكَتْ يَمِينُكَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ رَّقِيبًا
ከእነዚህ በኋላ እጅህ ከጨበጠቻቸው (ባሮች) በስተቀር ሴቶች ለአንተ አይፈቀዱልህም፡፡ ከሚስቶችም መልካቸው ቢደንቅህም እንኳ በእነርሱ ልታላውጥ (አይፈቀደልህም)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡
53يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَدْخُلُوا بُيُوتَ النَّبِيِّ إِلَّا أَن يُؤْذَنَ لَكُمْ إِلَىٰ طَعَامٍ غَيْرَ نَاظِرِينَ إِنَاهُ وَلَٰكِنْ إِذَا دُعِيتُمْ فَادْخُلُوا فَإِذَا طَعِمْتُمْ فَانتَشِرُوا وَلَا مُسْتَأْنِسِينَ لِحَدِيثٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكُمْ كَانَ يُؤْذِي النَّبِيَّ فَيَسْتَحْيِي مِنكُمْ ۖ وَاللَّهُ لَا يَسْتَحْيِي مِنَ الْحَقِّ ۚ وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَاسْأَلُوهُنَّ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ ۚ ذَٰلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ ۚ وَمَا كَانَ لَكُمْ أَن تُؤْذُوا رَسُولَ اللَّهِ وَلَا أَن تَنكِحُوا أَزْوَاجَهُ مِن بَعْدِهِ أَبَدًا ۚ إِنَّ ذَٰلِكُمْ كَانَ عِندَ اللَّهِ عَظِيمًا
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መድረሱን የማትጠባበቁ ስትኾኑ ወደ ምግብ ካልተፈቀደላችሁ በስተቀር የነቢዩን ቤቶች (በምንም ጊዜ) አትግቡ፡፡ ግን በተጠራችሁ ጊዜ ግቡ፡፡ በተመገባችሁም ጊዜ ወዲያውኑ ተበተኑ፡፡ ለወግ የምትጫወቱ ኾናችሁም (አትቆዩ)፡፡ ይህ ነቢዩን በእርግጥ ያስቸግራል፡፡ ከእናንተም ያፍራል፡፡ ግን አላህ ከእውነት አያፍርም፡፡ ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው፡፡ ይህ ለልቦቻችሁ፤ ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው፡፡ የአላህንም መልክተኛ ልታስቸግሩ ሚስቶቹንም ከእርሱ በኋላ ምንጊዜም ልታገቡ ለእናንተ አይገባችሁም፡፡ ይህ አላህ ዘንድ ከባድ (ኀጢአት) ነው፡፡
54إِن تُبْدُوا شَيْئًا أَوْ تُخْفُوهُ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት (በርሱ ይመነዳችኋል)፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
55لَّا جُنَاحَ عَلَيْهِنَّ فِي آبَائِهِنَّ وَلَا أَبْنَائِهِنَّ وَلَا إِخْوَانِهِنَّ وَلَا أَبْنَاءِ إِخْوَانِهِنَّ وَلَا أَبْنَاءِ أَخَوَاتِهِنَّ وَلَا نِسَائِهِنَّ وَلَا مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ ۗ وَاتَّقِينَ اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدًا
(የነቢዩ ሚስቶች) በአባቶቻቸው፣ በወንዶች ልጆቻቸውም፣ በወንድሞቻቸውም፣ ወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ በእኅቶቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ (ምእምናት በኾኑት) በሴቶቻቸውም፣ እጆቻቸው በጨበጧቸውም ባሮች (አጠገብ በመገለጥ) በእነርሱ ላይ ኃጢአት የለባቸውም፡፡ (ሴቶች ሆይ! ታዘዙ) አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነውና፡፡
56إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
አል-አህዛብቁርአን ማውጫ
73አንቀጽ
MedinanRevelation
54አንቀጽ

ትርጉም — አል-አህዛብ 54

ሱረቱ አል-አህዛብ አንቀጽ 54 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት (በርሱ ይመነዳችኋል)፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ…

ሱረቱ አንቀጽ 54/73 — ሱረቱ አል-አህዛብ الأحزاب (Medinan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ሱረቱ አል-አህዛብ ስሙ, ሱረቱ አል-አህዛብ ትርጉም, ሱረቱ አል-አህዛብ mp3, ሱረቱ አል-አህዛብ pdf. አንቀጽ 52–56. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Monday, September 7, 2026

Don't forget us in your sincere prayers