La sourate Al-Muddaththir en Amharique
يَا أَيُّهَا الْمُدَّثِّرُ(1) አንተ (ልብስህን) ደራቢው ሆይ! |
قُمْ فَأَنذِرْ(2) ተነሳ አስጠንቅቅም፡፡ |
وَرَبَّكَ فَكَبِّرْ(3) ጌታህንም አክብር፡፡ |
وَثِيَابَكَ فَطَهِّرْ(4) ልብስህንም አጥራ፡፡ |
وَالرُّجْزَ فَاهْجُرْ(5) ጣዖትንም ራቅ፡፡ |
وَلَا تَمْنُن تَسْتَكْثِرُ(6) ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ፤ (በረከትን) አትለግስለለ |
وَلِرَبِّكَ فَاصْبِرْ(7) ለጌታህም (ትዕዛዝ) ታገሥ፡፡ |
فَإِذَا نُقِرَ فِي النَّاقُورِ(8) በቀንዱም በተነፋ ጊዜ (ነገሩ ይበረታል)፡፡ |
فَذَٰلِكَ يَوْمَئِذٍ يَوْمٌ عَسِيرٌ(9) ይህም (ጊዜ) ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡ |
عَلَى الْكَافِرِينَ غَيْرُ يَسِيرٍ(10) በከሓዲዎች ላይ ገር ያልኾነ ነው፡፡ |
ذَرْنِي وَمَنْ خَلَقْتُ وَحِيدًا(11) አንድ ኾኖ ከፈጠርኩት ሰው ጋር ተዎኝ (እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ |
وَجَعَلْتُ لَهُ مَالًا مَّمْدُودًا(12) ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በያይነቱ) ያደረግሁለት፡፡ |
وَبَنِينَ شُهُودًا(13) (በያደባባዩ) ተገኝዎች የኾኑ ወንዶች ልጆችንም፡፡ |
وَمَهَّدتُّ لَهُ تَمْهِيدًا(14) ለእርሱም (ኑሮውን) መዘርጋትን የዘረጋሁለት (ከኾነ ሰው ገር ተዎኝ)፡፡ |
ثُمَّ يَطْمَعُ أَنْ أَزِيدَ(15) ከዚያም ልጨምርለት ይከጅላል፡፡ |
كَلَّا ۖ إِنَّهُ كَانَ لِآيَاتِنَا عَنِيدًا(16) ይከልከል፤ እርሱ ለአንቀጾቻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበር፡፡ |
سَأُرْهِقُهُ صَعُودًا(17) በእርግጥ ችግርን አስገድደዋለሁ፡፡ |
إِنَّهُ فَكَّرَ وَقَدَّرَ(18) እርሱ (በቁርኣን ነገር) ሐሰበ፤ ገመተም፡፡ |
فَقُتِلَ كَيْفَ قَدَّرَ(19) ተረገመም፤ እንዴት ገመተ! |
ثُمَّ قُتِلَ كَيْفَ قَدَّرَ(20) ከዚያም (ከሞት በኋላ) ተረገመ፡፡ እንዴት ገመተ! |
ثُمَّ نَظَرَ(21) ከዚያም እንደ ገና (በቁርኣኑ ነገር) ተመለከተ፡፡ |
ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ(22) ከዚያም ፊቱን አጨፈገገ፤ አኮማተረም፡፡ |
ثُمَّ أَدْبَرَ وَاسْتَكْبَرَ(23) ከዚያም (ከማመን) ዞረ፤ ኮራም፡፡ |
فَقَالَ إِنْ هَٰذَا إِلَّا سِحْرٌ يُؤْثَرُ(24) አለም «ይህ (ከሌላ) የሚቀዳ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ |
إِنْ هَٰذَا إِلَّا قَوْلُ الْبَشَرِ(25) «ይህ የሰው ቃል እንጅ ሌላ አይደለም፡፡» |
سَأُصْلِيهِ سَقَرَ(26) በሰቀር ውስጥ በእርግጥ አገባዋለሁ፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا سَقَرُ(27) ሰቀር ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? |
لَا تُبْقِي وَلَا تَذَرُ(28) (ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም አትተውምም፡፡ |
لَوَّاحَةٌ لِّلْبَشَرِ(29) ቆዳን በጣም አክሳይ ናት፡፡ |
عَلَيْهَا تِسْعَةَ عَشَرَ(30) በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት፡፡ |
وَمَا جَعَلْنَا أَصْحَابَ النَّارِ إِلَّا مَلَائِكَةً ۙ وَمَا جَعَلْنَا عِدَّتَهُمْ إِلَّا فِتْنَةً لِّلَّذِينَ كَفَرُوا لِيَسْتَيْقِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَيَزْدَادَ الَّذِينَ آمَنُوا إِيمَانًا ۙ وَلَا يَرْتَابَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَالْمُؤْمِنُونَ ۙ وَلِيَقُولَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ وَالْكَافِرُونَ مَاذَا أَرَادَ اللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلًا ۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ اللَّهُ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي مَن يَشَاءُ ۚ وَمَا يَعْلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَ ۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكْرَىٰ لِلْبَشَرِ(31) የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፡፡ እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ እርሷም (የሰቀር እሳት) ለሰዎች መገሰጫ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ |
كَلَّا وَالْقَمَرِ(32) (ከክህደት) ይከልከሉ፡፡ በጨረቃ እምላለሁ፡፡ |
وَاللَّيْلِ إِذْ أَدْبَرَ(33) በሌሊቱም በኼደ ጊዜ፡፡ |
وَالصُّبْحِ إِذَا أَسْفَرَ(34) በንጋቱም ባበራ ጊዜ፡፡ |
إِنَّهَا لَإِحْدَى الْكُبَرِ(35) እርሷ (ሰቀር) ከታላላቆቹ (አደጋዎች) አንዷ ናት፡፡ |
نَذِيرًا لِّلْبَشَرِ(36) ለሰዎች አስፈራሪ ስትኾን፡፡ |
لِمَن شَاءَ مِنكُمْ أَن يَتَقَدَّمَ أَوْ يَتَأَخَّرَ(37) ከእናንተ (ወደ በጎ ነገር) መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለሻ ሰው (አስፈራሪ ስትኾኑ)፡፡ |
كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ(38) ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡ |
إِلَّا أَصْحَابَ الْيَمِينِ(39) የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡ |
فِي جَنَّاتٍ يَتَسَاءَلُونَ(40) (እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡ |
عَنِ الْمُجْرِمِينَ(41) ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡ |
مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ(42) (ይሏቸዋልም) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?» |
قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ(43) (እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡ |
وَلَمْ نَكُ نُطْعِمُ الْمِسْكِينَ(44) «ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡ |
وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ الْخَائِضِينَ(45) «ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡ |
وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوْمِ الدِّينِ(46) «በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡ |
حَتَّىٰ أَتَانَا الْيَقِينُ(47) «እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡» |
فَمَا تَنفَعُهُمْ شَفَاعَةُ الشَّافِعِينَ(48) የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡ |
فَمَا لَهُمْ عَنِ التَّذْكِرَةِ مُعْرِضِينَ(49) ከግሣጼዬም (ከቁርኣን) የሚያፈገፍጉት ለእነርሱ ምን አልላቸው? |
كَأَنَّهُمْ حُمُرٌ مُّسْتَنفِرَةٌ(50) እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዮች ይመስላሉ፡፡ |
فَرَّتْ مِن قَسْوَرَةٍ(51) ከዐንበሳ የሸሹ፡፡ |
بَلْ يُرِيدُ كُلُّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُؤْتَىٰ صُحُفًا مُّنَشَّرَةً(52) ይልቁንም ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተዘረጉ ጽሑፎችን እንዲስሰጥ ይፈልጋል፡፡ |
كَلَّا ۖ بَل لَّا يَخَافُونَ الْآخِرَةَ(53) ይከልከሉ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) አይፈሩም፡፡ |
كَلَّا إِنَّهُ تَذْكِرَةٌ(54) ይከልከሉ፡፡ እርሱ (ቁርኣን) መገሠጫ ነው፡፡ |
فَمَن شَاءَ ذَكَرَهُ(55) ስለዚህ የሻ ሰው ይገሰጽበታል፡፡ |
وَمَا يَذْكُرُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ ۚ هُوَ أَهْلُ التَّقْوَىٰ وَأَهْلُ الْمَغْفِرَةِ(56) አላህም ካልሻ በስተቀር አይገሠጹም፡፡ እርሱ (አላህ) የመፈራት ባለቤት የምሕረትም ባለቤት ነው፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Muddaththir : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Muddaththir complète en haute qualité.
Ahmed Al Ajmy Bandar Balila Khalid Al Jalil Saad Al Ghamdi Saud Al Shuraim Abdul Basit Abdul Rashid Sufi Abdullah Basfar Abdullah Al Juhani Fares Abbad Maher Al Muaiqly Al Minshawi Al Hosary Mishari Al-afasi Yasser Al Dosari
Donnez-nous une invitation valide