ፋጢር · 37/45
ትርጉም ፊደሎች — ሱረቱ ፋጢር
وَهُمْ يَصْطَرِخُونَ فِيهَا رَبَّنَا أَخْرِجْنَا نَعْمَلْ صَالِحًا غَيْرَ الَّذِي كُنَّا نَعْمَلُ ۚ أَوَلَمْ نُعَمِّرْكُم مَّا يَتَذَكَّرُ فِيهِ مَن تَذَكَّرَ وَجَاءَكُمُ النَّذِيرُ ۖ فَذُوقُوا فَمَا لِلظَّالِمِينَ مِن نَّصِيرٍ ۝٣٧
Wa hum yastarikhoona feehaa Rabbanaa akhrijnaa na`mal saalihan ghairal lazee kunnaa na`mal; awa lamnu `ammirkum maa yatazak karu feehi man tazakkara wa jaaa`akumun nazeeru fazooqoo famaa lizzaalimeena min naseer
📖 በአማርኛ
እነርሱም በርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኀይል ይጮሃሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላ በጎ ሥራን እንሠራ ዘንድ አውጣን» (ይላሉ)፡፡ «በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰጽበትን ዕድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂውም መጥቶላችኋል (አስተባብላችኋልም)፡፡ ስለዚህ ቅመሱ፡፡ ለበደለኞችም ምንም ረዳት የላቸውም» (ይባላሉ)፡፡

🎧 ስሙ


📜 አንቀጽ 35-39 — ሱረቱ ፋጢር

35الَّذِي أَحَلَّنَا دَارَ الْمُقَامَةِ مِن فَضْلِهِ لَا يَمَسُّنَا فِيهَا نَصَبٌ وَلَا يَمَسُّنَا فِيهَا لُغُوبٌ
(እርሱም) ያ ከችሮታው የዘላለም መኖሪያን አገር ያሰፈረን ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከራ አይነካንም፡፡ በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካንም፡፡»
36وَالَّذِينَ كَفَرُوا لَهُمْ نَارُ جَهَنَّمَ لَا يُقْضَىٰ عَلَيْهِمْ فَيَمُوتُوا وَلَا يُخَفَّفُ عَنْهُم مِّنْ عَذَابِهَا ۚ كَذَٰلِكَ نَجْزِي كُلَّ كَفُورٍ
እነዚያ የካዱትም ለእነርሱ የገሀነም እሳት አልላቸው፡፡ ይሞቱ ዘንድ በእነርሱ ላይ (በሞት) አይፈረድም፡፡ ከቅጣቷም ከእነርሱ አይቀለልላቸውም፡፡ እንደዚሁ ከሓዲን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
37وَهُمْ يَصْطَرِخُونَ فِيهَا رَبَّنَا أَخْرِجْنَا نَعْمَلْ صَالِحًا غَيْرَ الَّذِي كُنَّا نَعْمَلُ ۚ أَوَلَمْ نُعَمِّرْكُم مَّا يَتَذَكَّرُ فِيهِ مَن تَذَكَّرَ وَجَاءَكُمُ النَّذِيرُ ۖ فَذُوقُوا فَمَا لِلظَّالِمِينَ مِن نَّصِيرٍ
እነርሱም በርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኀይል ይጮሃሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላ በጎ ሥራን እንሠራ ዘንድ አውጣን» (ይላሉ)፡፡ «በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰጽበትን ዕድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂውም መጥቶላችኋል (አስተባብላችኋልም)፡፡ ስለዚህ ቅመሱ፡፡ ለበደለኞችም ምንም ረዳት የላቸውም» (ይባላሉ)፡፡
38إِنَّ اللَّهَ عَالِمُ غَيْبِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ
አላህ የሰማያትንና የምድርን ምስጢር በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
39هُوَ الَّذِي جَعَلَكُمْ خَلَائِفَ فِي الْأَرْضِ ۚ فَمَن كَفَرَ فَعَلَيْهِ كُفْرُهُ ۖ وَلَا يَزِيدُ الْكَافِرِينَ كُفْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ إِلَّا مَقْتًا ۖ وَلَا يَزِيدُ الْكَافِرِينَ كُفْرُهُمْ إِلَّا خَسَارًا
እርሱ ያ በምድር ውስጥ ምትኮች ያደረጋችሁ ነው፡፡ የካደም ሰው ክህደቱ በእርሱው ላይ ብቻ ነው፡፡ ከሓዲዎችንም ክሕደታቸው ከጌታቸው ዘንድ መጠላትን እንጂ ሌላ አይጨመርላቸውም፡፡ ከሓዲዎችንም ክሕደታቸው ከሳራን እንጂ አይጨምርላቸውም፡፡
ፋጢርቁርአን ማውጫ
45አንቀጽ
MeccanRevelation
37አንቀጽ

ትርጉም — ፋጢር 37

ሱረቱ ፋጢር አንቀጽ 37 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : እነርሱም በርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኀይል ይጮሃሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ…

ሱረቱ አንቀጽ 37/45 — ሱረቱ ፋጢር فاطر (Meccan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ሱረቱ ፋጢር ስሙ, ሱረቱ ፋጢር ትርጉም, ሱረቱ ፋጢር mp3, ሱረቱ ፋጢር pdf. አንቀጽ 35–39. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, September 8, 2026

Don't forget us in your sincere prayers