አል-አንአም · 159/165
ትርጉም ፊደሎች — አል-አንአም
إِنَّ الَّذِينَ فَرَّقُوا دِينَهُمْ وَكَانُوا شِيَعًا لَّسْتَ مِنْهُمْ فِي شَيْءٍ ۚ إِنَّمَا أَمْرُهُمْ إِلَى اللَّهِ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُوا يَفْعَلُونَ ۝١٥٩
Innal lazeena farraqoo deenahum wa kaanoo shiya`allasta minhum fee shai`; innamaaa amruhum ilallaahi summma yunabbi`uhum bimaa kaanoo yaf`aloon
📖 በአማርኛ
እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አሕዛብም የኾኑ በምንም ከእነሱ አይደለህም፡፡ ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ ይነገራቸዋል፡፡
🎧 ስሙ

📜 አንቀጽ 157-161 — አል-አንአም

157أَوْ تَقُولُوا لَوْ أَنَّا أُنزِلَ عَلَيْنَا الْكِتَابُ لَكُنَّا أَهْدَىٰ مِنْهُمْ ۚ فَقَدْ جَاءَكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ ۚ فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن كَذَّبَ بِآيَاتِ اللَّهِ وَصَدَفَ عَنْهَا ۗ سَنَجْزِي الَّذِينَ يَصْدِفُونَ عَنْ آيَاتِنَا سُوءَ الْعَذَابِ بِمَا كَانُوا يَصْدِفُونَ
ወይም «እኛ መጽሐፍ በእኛ ላይ በተወረደ ኖሮ ከእነሱ ይበልጥ የተመራን እንኾን ነበር» እንዳትሉ ነው፡፡ ስለዚህ ከጌታችሁ ግልጽ ማስረጃ፣ መምሪያም፣ እዝነትም በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ በአላህም አንቀጾች ካስተባበለና ከእርሷም ከዞረ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነዚያን አንቀጾቻችንን የሚተውትን ይተውት በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እንቀጣቸዋለን፡፡
158هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا أَن تَأْتِيَهُمُ الْمَلَائِكَةُ أَوْ يَأْتِيَ رَبُّكَ أَوْ يَأْتِيَ بَعْضُ آيَاتِ رَبِّكَ ۗ يَوْمَ يَأْتِي بَعْضُ آيَاتِ رَبِّكَ لَا يَنفَعُ نَفْسًا إِيمَانُهَا لَمْ تَكُنْ آمَنَتْ مِن قَبْلُ أَوْ كَسَبَتْ فِي إِيمَانِهَا خَيْرًا ۗ قُلِ انتَظِرُوا إِنَّا مُنتَظِرُونَ
መላእክት ልትመጣላቸው ወይም ጌታህ (ቅጣቱ) ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ይጠባበቃሉን ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ በሚመጣ ቀን ከዚህ በፊት አማኝ ያልኾነችን ነፍስ እምነትዋ ወይም በእምነትዋ (ጊዜ) በጎ ያልሠራችን (ነፍስ ጸጸትዋ) አይጠቅማትም፡፡ ተጠባበቁ እኛ ተጠባባቂዎች ነንና በላቸው፡፡
159إِنَّ الَّذِينَ فَرَّقُوا دِينَهُمْ وَكَانُوا شِيَعًا لَّسْتَ مِنْهُمْ فِي شَيْءٍ ۚ إِنَّمَا أَمْرُهُمْ إِلَى اللَّهِ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُوا يَفْعَلُونَ
እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አሕዛብም የኾኑ በምንም ከእነሱ አይደለህም፡፡ ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ ይነገራቸዋል፡፡
160مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
161قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል፡፡
አል-አንአምቁርአን ማውጫ
165አንቀጽ
MeccanRevelation
159አንቀጽ

ትርጉም — አል-አንአም 159

ሱረቱ አል-አንአም አንቀጽ 159 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አሕዛብም የኾኑ በምንም ከእነሱ አይደለህም፡፡ ነገራቸው ወደ…

ሱረቱ አንቀጽ 159/165 — አል-አንአም الأنعام (Meccan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: አል-አንአም ስሙ, አል-አንአም ትርጉም, አል-አንአም mp3, አል-አንአም pdf. አንቀጽ 157–161. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers