La sourate Ar-Rahman en Amharique
الرَّحْمَٰنُ(1) አል-ረሕማን፤ |
عَلَّمَ الْقُرْآنَ(2) ቁርኣንን አስተማረ፡፡ |
خَلَقَ الْإِنسَانَ(3) ሰውን ፈጠረ፡፡ |
عَلَّمَهُ الْبَيَانَ(4) መናገርን አስተማረው፡፡ |
الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ بِحُسْبَانٍ(5) ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡ |
وَالنَّجْمُ وَالشَّجَرُ يَسْجُدَانِ(6) ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡ |
وَالسَّمَاءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ الْمِيزَانَ(7) ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡ |
أَلَّا تَطْغَوْا فِي الْمِيزَانِ(8) በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡ |
وَأَقِيمُوا الْوَزْنَ بِالْقِسْطِ وَلَا تُخْسِرُوا الْمِيزَانَ(9) መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡ |
وَالْأَرْضَ وَضَعَهَا لِلْأَنَامِ(10) ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡ |
فِيهَا فَاكِهَةٌ وَالنَّخْلُ ذَاتُ الْأَكْمَامِ(11) በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡ |
وَالْحَبُّ ذُو الْعَصْفِ وَالرَّيْحَانُ(12) የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(13) (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
خَلَقَ الْإِنسَانَ مِن صَلْصَالٍ كَالْفَخَّارِ(14) ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡ |
وَخَلَقَ الْجَانَّ مِن مَّارِجٍ مِّن نَّارٍ(15) ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(16) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
رَبُّ الْمَشْرِقَيْنِ وَرَبُّ الْمَغْرِبَيْنِ(17) የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(18) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
مَرَجَ الْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِيَانِ(19) ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡ |
بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لَّا يَبْغِيَانِ(20) (እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(21) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?› |
يَخْرُجُ مِنْهُمَا اللُّؤْلُؤُ وَالْمَرْجَانُ(22) ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(23) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
وَلَهُ الْجَوَارِ الْمُنشَآتُ فِي الْبَحْرِ كَالْأَعْلَامِ(24) እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(25) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ(26) በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ |
وَيَبْقَىٰ وَجْهُ رَبِّكَ ذُو الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ(27) የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(28) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
يَسْأَلُهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ كُلَّ يَوْمٍ هُوَ فِي شَأْنٍ(29) በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(30) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?› |
سَنَفْرُغُ لَكُمْ أَيُّهَ الثَّقَلَانِ(31) እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(32) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ إِنِ اسْتَطَعْتُمْ أَن تَنفُذُوا مِنْ أَقْطَارِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ فَانفُذُوا ۚ لَا تَنفُذُونَ إِلَّا بِسُلْطَانٍ(33) የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም) |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(34) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
يُرْسَلُ عَلَيْكُمَا شُوَاظٌ مِّن نَّارٍ وَنُحَاسٌ فَلَا تَنتَصِرَانِ(35) በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(36) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
فَإِذَا انشَقَّتِ السَّمَاءُ فَكَانَتْ وَرْدَةً كَالدِّهَانِ(37) ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(38) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُسْأَلُ عَن ذَنبِهِ إِنسٌ وَلَا جَانٌّ(39) በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(40) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
يُعْرَفُ الْمُجْرِمُونَ بِسِيمَاهُمْ فَيُؤْخَذُ بِالنَّوَاصِي وَالْأَقْدَامِ(41) ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(42) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡ |
هَٰذِهِ جَهَنَّمُ الَّتِي يُكَذِّبُ بِهَا الْمُجْرِمُونَ(43) ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡ |
يَطُوفُونَ بَيْنَهَا وَبَيْنَ حَمِيمٍ آنٍ(44) በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(45) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ(46) በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(47) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
ذَوَاتَا أَفْنَانٍ(48) የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(49) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
فِيهِمَا عَيْنَانِ تَجْرِيَانِ(50) በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(51) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
فِيهِمَا مِن كُلِّ فَاكِهَةٍ زَوْجَانِ(52) በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(53) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
مُتَّكِئِينَ عَلَىٰ فُرُشٍ بَطَائِنُهَا مِنْ إِسْتَبْرَقٍ ۚ وَجَنَى الْجَنَّتَيْنِ دَانٍ(54) የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(55) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
فِيهِنَّ قَاصِرَاتُ الطَّرْفِ لَمْ يَطْمِثْهُنَّ إِنسٌ قَبْلَهُمْ وَلَا جَانٌّ(56) በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(57) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
كَأَنَّهُنَّ الْيَاقُوتُ وَالْمَرْجَانُ(58) ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(59) ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
هَلْ جَزَاءُ الْإِحْسَانِ إِلَّا الْإِحْسَانُ(60) የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን? |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(61) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
وَمِن دُونِهِمَا جَنَّتَانِ(62) ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(63) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?› |
مُدْهَامَّتَانِ(64) ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(65) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
فِيهِمَا عَيْنَانِ نَضَّاخَتَانِ(66) በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(67) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
فِيهِمَا فَاكِهَةٌ وَنَخْلٌ وَرُمَّانٌ(68) በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(69) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
فِيهِنَّ خَيْرَاتٌ حِسَانٌ(70) በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(71) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
حُورٌ مَّقْصُورَاتٌ فِي الْخِيَامِ(72) በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(73) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
لَمْ يَطْمِثْهُنَّ إِنسٌ قَبْلَهُمْ وَلَا جَانٌّ(74) ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(75) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ? |
مُتَّكِئِينَ عَلَىٰ رَفْرَفٍ خُضْرٍ وَعَبْقَرِيٍّ حِسَانٍ(76) በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡ |
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ(77) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? |
تَبَارَكَ اسْمُ رَبِّكَ ذِي الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ(78) የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Ar-Rahman : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Ar-Rahman complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide