فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ٦٥
🔤 Transliteration
Falaa wa Rabbika laa yu`minoona hattaa yuhakkimooka fe emaa shajara bainahum summa laa yajidoo fee anfusihim harajam mimmaa qadaita wa yusal limoo tasleemaa
📖 ትርጉም (በአማርኛ)
📖 በአማርኛ
በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡
የቃላት ማብራሪያ፦ فَلَا وَرَبِّكَ : ይህ አገላለጽ በአላህ ማለት (ቃሰም) ነው፤ "فلا" የሚለው ቃል ቀደም ያሉትን ንግግሮች ውድቅ ለማድረግ የመጣ ነው።يُحَكِّمُوكَ : እንዲፈርዱልን/አንተን ፈራጅ አድርገው እንዲቀበሉህ ማለት ነው።شَجَرَ بَيْنَهُمْ : በመካከላቸው የተፈጠረ አለመግባባትና ክርክር ማለት ነው።حَرَجًا : ጭንቀት፣ ጠባበነት ወይም ቅሬታ ማለት ነው።يُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا : ሙሉ በሙሉ በመገዛትና በመቀበል ማለት ነው።የአንቀጹ ትርጉምና ማብራሪያ፦ አላህ ራሱን በመማለል እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ እነዚህ ሰዎች በእውነት አማኞች አይደሉም። እምነታቸው ትክክለኛና ጸንቶ የሚቆይ አይሆንም፤ እስከ አንተ (የአላህ መልእክተኛ) በመካከላቸው በተፈጠረው ክርክርና አለመግባባት ሁሉ ፈራጅ አድርገው እስኪቀበሉህ ድረስ። ይህ ማለት በሕይወትህ ጊዜ ወደ አንተ፣ ከሞትህ በኋላ ደግሞ ወደ ሰርዓትህ (ሱናህ) በመመለስ በመካከላቸው የሚፈጠረውን አለመግባባት ሁሉ በአንተ ፍርድ መፍታት አለባቸው ማለት ነው።
ከዚያም በአንተ ፍርድ ልቦቻቸው ምንም ጭንቀት፣ ጠባበነት ወይም ቅሬታ ሳያገኙ ሙሉ በሙሉ በልብም በአካልም ተገዝተው መቀበል አለባቸው። ይህ የእምነት መሠረት ነው።
እንግዲህ እውነተኛ እምነት የአላህ መልእክተኛ የፈረደውን በሙሉ ልብ መቀበልንና በዚያ መረካትን ይጠይቃል። ልባችን በፍርዱ ላይ ጠባበነት ካለው፣ ወይም ከወደድነው ብቻ ተቀብለን የማንወደውን ካልተቀበልን፣ እምነታችን የተበላሸ ነው። ነገር ግን የአላህ ሕግ ሁልጊዜ ለሰው ልጅ ጥቅምና ፍትሕን ያመጣል፤ ምክንያቱም ፈጣሪያችን ከሁሉ በላይ የሚያውቀንና የሚጠብቀን ነው። ስለዚህ በፍቅርና በደስታ በመገዛት የአላህን ፍርድ እንቀበል፤ ይህም የእምነታችን ማረጋገጫና የልባችን መድኃኒት ነው።
فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤۡمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيۡنَهُمۡ ثُمَّ لَا يَجِدُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيۡتَ وَيُسَلِّمُواْ تَسۡلِيمًا ٦٥
በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡
🖼️ Save Image
🎬 Save Video
📜 አንቀጽ 63-67 — ሱረቱ አን-ኒሳ
63 أُولَٰئِكَ الَّذِينَ يَعْلَمُ اللَّهُ مَا فِي قُلُوبِهِمْ فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ وَعِظْهُمْ وَقُل لَّهُمْ فِي أَنفُسِهِمْ قَوْلًا بَلِيغًا
እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡ እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡
64 وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَلَوْ أَنَّهُمْ إِذ ظَّلَمُوا أَنفُسَهُمْ جَاءُوكَ فَاسْتَغْفَرُوا اللَّهَ وَاسْتَغْفَرَ لَهُمُ الرَّسُولُ لَوَجَدُوا اللَّهَ تَوَّابًا رَّحِيمًا
ማንንም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጅ አልላክንም፡፡ እነሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ ቢመጡና አላህንም ምሕረትን በለመኑ መልክተኛውም ለነርሱ ምሕረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ኾኖ ባገኙት ነበር፡፡
65 فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡
66 وَلَوْ أَنَّا كَتَبْنَا عَلَيْهِمْ أَنِ اقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ أَوِ اخْرُجُوا مِن دِيَارِكُم مَّا فَعَلُوهُ إِلَّا قَلِيلٌ مِّنْهُمْ ۖ وَلَوْ أَنَّهُمْ فَعَلُوا مَا يُوعَظُونَ بِهِ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ وَأَشَدَّ تَثْبِيتًا
እኛም በእነርሱ ላይ፡- «ነፍሶቻችሁን ግደሉ ወይም ከአገሮቻችሁ ውጡ» ማለትን በጻፍን ኖሮ ከነሱ ጥቂቶቹ እንጅ ባልሠሩት ነበር፡፡ እነርሱም በእርሱ የሚገሰጹበትን ነገር በሠሩ ኖሮ ለነሱ መልካምና (በእምነታቸው ላይ) ለመርጋትም በጣም የበረታ በኾነ ነበር፡፡
67 وَإِذًا لَّآتَيْنَاهُم مِّن لَّدُنَّا أَجْرًا عَظِيمًا
ያን ጊዜም ከእኛ ዘንድ ታላቅን ምንዳ በሰጠናቸው ነበር፡፡
ትርጉም — አን-ኒሳ 65 ሱረቱ አን-ኒሳ አንቀጽ 65 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው…
ሱረቱ አንቀጽ 65/176 — ሱረቱ አን-ኒሳ النساء (Medinan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ሱረቱ አን-ኒሳ ስሙ, ሱረቱ አን-ኒሳ ትርጉም, ሱረቱ አን-ኒሳ mp3, ሱረቱ አን-ኒሳ pdf. አንቀጽ 63–67. በአማርኛ: العربية.