ኢብራሂም · 38/52
ትርጉም ፊደሎች — ኢብራሂም
رَبَّنَا إِنَّكَ تَعْلَمُ مَا نُخْفِي وَمَا نُعْلِنُ ۗ وَمَا يَخْفَىٰ عَلَى اللَّهِ مِن شَيْءٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي السَّمَاءِ ۝٣٨
Rabbanaaa innaka ta`lamu maa nukhfee wa maa nu`lin; wa maa yakhfaa `alal laahi min shai`in fil ardi wa laa fis samaaa
📖 በአማርኛ
«ጌታችን ሆይ! አንተ የምንደብቀውንም የምንገልጸውንም ሁሉ በእርግጥ ታውቃለህ፡፡ በአላህም ላይ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር አይደበቅም፡፡
🎧 ስሙ

📜 አንቀጽ 36-40 — ኢብራሂም

36رَبِّ إِنَّهُنَّ أَضْلَلْنَ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ ۖ فَمَن تَبِعَنِي فَإِنَّهُ مِنِّي ۖ وَمَنْ عَصَانِي فَإِنَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
«ጌታዬ ሆይ! እነርሱ (ጣዖታት) ከሰዎች ብዙዎችን አሳስተዋልና፡፡ የተከተለኝም ሰው እርሱ ከኔ ነው፡፡ ትእዛዜንም የጣሰ ሰው አንተ መሓሪ አዛኝ ነህ፡፡
37رَّبَّنَا إِنِّي أَسْكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِي بِوَادٍ غَيْرِ ذِي زَرْعٍ عِندَ بَيْتِكَ الْمُحَرَّمِ رَبَّنَا لِيُقِيمُوا الصَّلَاةَ فَاجْعَلْ أَفْئِدَةً مِّنَ النَّاسِ تَهْوِي إِلَيْهِمْ وَارْزُقْهُم مِّنَ الثَّمَرَاتِ لَعَلَّهُمْ يَشْكُرُونَ
«ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት (በካዕባ) አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ፡፡ ጌታችን ሆይ! ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ (አስቀመጥኳቸው)፡፡ ከሰዎችም ልቦችን ወደእነሱ የሚናፍቁ አድርግ፡፡ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው፡፡
38رَبَّنَا إِنَّكَ تَعْلَمُ مَا نُخْفِي وَمَا نُعْلِنُ ۗ وَمَا يَخْفَىٰ عَلَى اللَّهِ مِن شَيْءٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي السَّمَاءِ
«ጌታችን ሆይ! አንተ የምንደብቀውንም የምንገልጸውንም ሁሉ በእርግጥ ታውቃለህ፡፡ በአላህም ላይ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር አይደበቅም፡፡
39الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي وَهَبَ لِي عَلَى الْكِبَرِ إِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ ۚ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ
«ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና፡፡
40رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ
«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ፤
ኢብራሂምቁርአን ማውጫ
52አንቀጽ
MeccanRevelation
38አንቀጽ

ትርጉም — ኢብራሂም 38

ሱረቱ ኢብራሂም አንቀጽ 38 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : «ጌታችን ሆይ! አንተ የምንደብቀውንም የምንገልጸውንም ሁሉ በእርግጥ ታውቃለህ፡፡ በአላህም ላይ…

ሱረቱ አንቀጽ 38/52 — ኢብራሂም إبراهيم (Meccan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ኢብራሂም ስሙ, ኢብራሂም ትርጉም, ኢብራሂም mp3, ኢብራሂም pdf. አንቀጽ 36–40. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers