አል-አንአም · 59/165
ትርጉም ፊደሎች — አል-አንአም
۞ وَعِندَهُ مَفَاتِحُ الْغَيْبِ لَا يَعْلَمُهَا إِلَّا هُوَ ۚ وَيَعْلَمُ مَا فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ ۚ وَمَا تَسْقُطُ مِن وَرَقَةٍ إِلَّا يَعْلَمُهَا وَلَا حَبَّةٍ فِي ظُلُمَاتِ الْأَرْضِ وَلَا رَطْبٍ وَلَا يَابِسٍ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ ۝٥٩
Wa `indahoo mafaatihul ghaibi laa ya`lamuhaaa illaa Hoo; wa ya`lamu maa fil barri walbahr; wa maa tasqutu minw waraqatin illaa ya`lamuhaa wa laa habbatin fee zulumaatil ardi wa laa ratbinw wa laa yaabisin illaa fee Kitaabim Mubeen
📖 በአማርኛ
የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም፡፡ በየብስና በባሕር ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ከቅጠልም አንዲትም አትረግፍም የሚያውቃት ቢኾን እንጅ፡፡ ከቅንጣትም በመሬት ጨለማዎች ውስጥ የለም ከእርጥብም ከደረቅም አንድም የለም ግልጽ በኾነው መጽሐፍ ውሰጥ (የተመዘገበ) ቢኾን እንጅ፡፡
🎧 ስሙ

📜 አንቀጽ 57-61 — አል-አንአም

57قُلْ إِنِّي عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّي وَكَذَّبْتُم بِهِ ۚ مَا عِندِي مَا تَسْتَعْجِلُونَ بِهِ ۚ إِنِ الْحُكْمُ إِلَّا لِلَّهِ ۖ يَقُصُّ الْحَقَّ ۖ وَهُوَ خَيْرُ الْفَاصِلِينَ
«እኔ ከጌታዬ በኾነች ግልጽ ማስረጃ ላይ ነኝ፡፡ በእርሱም አስተባበላችሁ፡፡ በርሱ የምትቻኮሉበት ቅጣት እኔ ዘንድ አይደለም፡፡ ፍርዱ ለአላህ ብቻ ነው፡፡ እውነትን ይፈርዳል፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው፡፡
58قُل لَّوْ أَنَّ عِندِي مَا تَسْتَعْجِلُونَ بِهِ لَقُضِيَ الْأَمْرُ بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ ۗ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِالظَّالِمِينَ
«በእርሱ የምትቻኮሉበት ቅጣት እኔ ዘንድ በኾነ ኖሮ በእኔና በእናንተ መካከል ነገሩ (ቅጣታችሁ) በተፈጸመ ነበር፡፡ አላህም በደለኞችን ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
59۞ وَعِندَهُ مَفَاتِحُ الْغَيْبِ لَا يَعْلَمُهَا إِلَّا هُوَ ۚ وَيَعْلَمُ مَا فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ ۚ وَمَا تَسْقُطُ مِن وَرَقَةٍ إِلَّا يَعْلَمُهَا وَلَا حَبَّةٍ فِي ظُلُمَاتِ الْأَرْضِ وَلَا رَطْبٍ وَلَا يَابِسٍ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ
የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም፡፡ በየብስና በባሕር ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ከቅጠልም አንዲትም አትረግፍም የሚያውቃት ቢኾን እንጅ፡፡ ከቅንጣትም በመሬት ጨለማዎች ውስጥ የለም ከእርጥብም ከደረቅም አንድም የለም ግልጽ በኾነው መጽሐፍ ውሰጥ (የተመዘገበ) ቢኾን እንጅ፡፡
60وَهُوَ الَّذِي يَتَوَفَّاكُم بِاللَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِالنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰ أَجَلٌ مُّسَمًّى ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
እርሱም ያ በሌሊት የሚያስተኛችሁ በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ (በቀን) ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡
61وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ ۖ وَيُرْسِلُ عَلَيْكُمْ حَفَظَةً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ
እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን ሁሉን አሸነፊ ነው፡፡ በናንተም ላይ ጠባቂዎችን (መላእክት) ይልካል፡፡ አንዳችሁንም ሞት በመጣበት ጊዜ (የሞት) መልእክተኞቻችን እነርሱ (ትእዛዛትን) የማያጓድሉ ሲኾኑ ይገድሉታል፡፡
አል-አንአምቁርአን ማውጫ
165አንቀጽ
MeccanRevelation
59አንቀጽ

ትርጉም — አል-አንአም 59

ሱረቱ አል-አንአም አንቀጽ 59 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም፡፡…

ሱረቱ አንቀጽ 59/165 — አል-አንአም الأنعام (Meccan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: አል-አንአም ስሙ, አል-አንአም ትርጉም, አል-አንአም mp3, አል-አንአም pdf. አንቀጽ 57–61. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers