ፋጢር · 16/45
ትርጉም ፊደሎች — ፋጢር
إِن يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ وَيَأْتِ بِخَلْقٍ جَدِيدٍ ۝١٦
Iny yashaa yuzhibkum wa yaati bikhalqin jadeed
📖 በአማርኛ
ቢሻ ያስወግዳችኋል፡፡ አዲስንም ፍጡር ያመጣል፡፡
🎧 ስሙ

📜 አንቀጽ 14-18 — ፋጢር

14إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا مَا اسْتَجَابُوا لَكُمْ ۖ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ ۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ
ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡
15۞ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡
16إِن يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ وَيَأْتِ بِخَلْقٍ جَدِيدٍ
ቢሻ ያስወግዳችኋል፡፡ አዲስንም ፍጡር ያመጣል፡፡
17وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ بِعَزِيزٍ
ይህም በአላህ ላይ ምንም አስቸጋሪ አይደለም፡፡
18وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ۚ وَإِن تَدْعُ مُثْقَلَةٌ إِلَىٰ حِمْلِهَا لَا يُحْمَلْ مِنْهُ شَيْءٌ وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰ ۗ إِنَّمَا تُنذِرُ الَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِالْغَيْبِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ ۚ وَمَن تَزَكَّىٰ فَإِنَّمَا يَتَزَكَّىٰ لِنَفْسِهِ ۚ وَإِلَى اللَّهِ الْمَصِيرُ
ኀጢአትን ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላዋን ሸክም አትሸከምም፡፡ የተከበደችም (ነፍስ) ወደ ሸክሟ ብትጣራ (ተጠሪው) የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢኾንም እንኳ ከእርሷ አንዳችን የሚሸከምላት አታገኝም፡፡ የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፡፡ የተጥራራም ሰው የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡
ፋጢርቁርአን ማውጫ
45አንቀጽ
MeccanRevelation
16አንቀጽ

ትርጉም — ፋጢር 16

ሱረቱ ፋጢር አንቀጽ 16 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : ቢሻ ያስወግዳችኋል፡፡ አዲስንም ፍጡር ያመጣል፡፡

ሱረቱ አንቀጽ 16/45 — ፋጢር فاطر (Meccan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ፋጢር ስሙ, ፋጢር ትርጉም, ፋጢር mp3, ፋጢር pdf. አንቀጽ 14–18. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers