PDF —
182 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አስ-ሳፋት pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አስ-ሳፋት pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አስ-ሳፋት ትርጉም. ሱረቱ አስ-ሳፋት (Meccan) 182 አንቀጽ.

← ያሲንሱረቱ አስ-ሳፋት ሳድ →


182 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭑﭒﭓ
37:1 መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡
ﭔﭕﭖ
37:2 መገሠጽንም በሚገሥጹት፤
ﭗﭘﭙ
37:3 ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡
ﭚﭛﭜﭝ
37:4 አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡
ﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥ
37:5 የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬ
37:6 እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡
ﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
37:7 አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼ
37:8 ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡
ﭽﭾﭿﮀﮁﮂ
37:9 የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡
ﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊ
37:10 ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡
ﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘ
37:11 ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡
ﮙﮚﮛﮜ
37:12 ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡
ﮝﮞﮟﮠﮡ
37:13 በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡
ﮢﮣﮤﮥﮦ
37:14 ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡
ﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭ
37:15 ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
ﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖ
37:16 «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?
ﯗﯘﯙ
37:17 «የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡
ﯚﯛﯜﯝﯞ
37:18 «አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡
ﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦ
37:19 እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡
ﯧﯨﯩﯪﯫﯬ
37:20 «ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡
ﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴ
37:21 «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡
ﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽ
37:22 (ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡
ﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅ
37:23 «ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡
ﰆﰇﰈﰉﰊ
37:24 «አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
37:25 (ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡
ﭖﭗﭘﭙﭚ
37:26 በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡
ﭛﭜﭝﭞﭟﭠ
37:27 የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡
ﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧ
37:28 (ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡
ﭨﭩﭪﭫﭬﭭ
37:29 (አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡
ﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹ
37:30 «ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡
ﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁ
37:31 «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡
ﮂﮃﮄﮅﮆ
37:32 «ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡
ﮇﮈﮉﮊﮋﮌ
37:33 ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡
ﮍﮎﮏﮐﮑ
37:34 እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡
ﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜ
37:35 እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡
ﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣ
37:36 እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡
ﮤﮥﮦﮧﮨﮩ
37:37 አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡
ﮪﮫﮬﮭﮮ
37:38 እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡
ﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖ
37:39 ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡
ﯗﯘﯙﯚﯛ
37:40 ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡
ﯜﯝﯞﯟﯠ
37:41 እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡
ﯡﯢﯣﯤ
37:42 ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤
ﯥﯦﯧﯨ
37:43 በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡
ﯩﯪﯫﯬ
37:44 ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡
ﯭﯮﯯﯰﯱﯲ
37:45 ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡
ﯳﯴﯵﯶ
37:46 ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡
ﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾ
37:47 በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡
ﯿﰀﰁﰂﰃ
37:48 እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡
ﰄﰅﰆﰇ
37:49 እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡
ﰈﰉﰊﰋﰌﰍ
37:50 የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡
ﰎﰏﰐﰑﰒﰓﰔﰕ
37:51 ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
37:52 «በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡
ﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝ
37:53 «በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡
ﭞﭟﭠﭡﭢ
37:54 እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨ
37:55 ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡
ﭩﭪﭫﭬﭭﭮ
37:56 ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡
ﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵ
37:57 «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡»
ﭶﭷﭸﭹ
37:58 (የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን?
ﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀ
37:59 «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡
ﮁﮂﮃﮄﮅﮆ
37:60 ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
ﮇﮈﮉﮊﮋ
37:61 ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡
ﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒ
37:62 በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
ﮓﮔﮕﮖﮗ
37:63 እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡
ﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞ
37:64 እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡
ﮟﮠﮡﮢﮣ
37:65 እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡
ﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
37:66 እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡
ﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓ
37:67 ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡
ﯔﯕﯖﯗﯘﯙ
37:68 ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡
ﯚﯛﯜﯝﯞ
37:69 እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡
ﯟﯠﯡﯢﯣ
37:70 እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡
ﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
37:71 ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡
ﯪﯫﯬﯭﯮ
37:72 በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡
ﯯﯰﯱﯲﯳﯴ
37:73 የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
ﯵﯶﯷﯸﯹ
37:74 ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
ﯺﯻﯼﯽﯾﯿ
37:75 ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን!
ﰀﰁﰂﰃﰄﰅ
37:76 እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
37:77 ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤
ﭖﭗﭘﭙﭚ
37:78 በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡
ﭛﭜﭝﭞﭟﭠ
37:79 «በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡»
ﭡﭢﭣﭤﭥ
37:80 እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪ
37:81 እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡
ﭫﭬﭭﭮ
37:82 ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡
ﭯﭰﭱﭲﭳﭴ
37:83 ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡
ﭵﭶﭷﭸﭹﭺ
37:84 ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡
ﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁ
37:85 «ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡
ﮂﮃﮄﮅﮆﮇ
37:86 «ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?
ﮈﮉﮊﮋﮌ
37:87 «በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡
ﮍﮎﮏﮐﮑ
37:88 በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡
ﮒﮓﮔﮕ
37:89 «እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡
ﮖﮗﮘﮙ
37:90 ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡
ﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠ
37:91 ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?»
ﮡﮢﮣﮤﮥ
37:92 «የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?»
ﮦﮧﮨﮩﮪ
37:93 በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡
ﮫﮬﮭﮮ
37:94 ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡
ﮯﮰﮱﯓﯔ
37:95 አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?»
ﯕﯖﯗﯘﯙ
37:96 «አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡»
ﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡ
37:97 «ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡
ﯢﯣﯤﯥﯦﯧ
37:98 በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡
ﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮ
37:99 አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»
ﯯﯰﯱﯲﯳﯴ
37:100 ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡
ﯵﯶﯷﯸ
37:101 ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡
ﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎﰏﰐﰑﰒﰓﰔﰕ
37:102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
37:103 ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡
ﭖﭗﭘﭙ
37:104 ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!
ﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
37:105 ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨ
37:106 ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡
ﭩﭪﭫﭬ
37:107 በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡
ﭭﭮﭯﭰﭱ
37:108 በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡
ﭲﭳﭴﭵ
37:109 ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡
ﭶﭷﭸﭹ
37:110 እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
ﭺﭻﭼﭽﭾ
37:111 እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡
ﭿﮀﮁﮂﮃﮄ
37:112 በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡
ﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
37:113 በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖ
37:114 በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡
ﮗﮘﮙﮚﮛﮜ
37:115 እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡
ﮝﮞﮟﮠﮡ
37:116 ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡
ﮢﮣﮤﮥ
37:117 በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡
ﮦﮧﮨﮩ
37:118 ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡
ﮪﮫﮬﮭﮮ
37:119 በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡
ﮯﮰﮱﯓﯔ
37:120 ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡
ﯕﯖﯗﯘﯙ
37:121 እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
ﯚﯛﯜﯝﯞ
37:122 ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡
ﯟﯠﯡﯢﯣ
37:123 ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
ﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
37:124 ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን?
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯ
37:125 በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን?
ﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
37:126 አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)?
ﭑﭒﭓﭔ
37:127 አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡
ﭕﭖﭗﭘﭙ
37:128 ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
ﭚﭛﭜﭝﭞ
37:129 በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡
ﭟﭠﭡﭢﭣ
37:130 ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡
ﭤﭥﭦﭧﭨ
37:131 እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
ﭩﭪﭫﭬﭭ
37:132 እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡
ﭮﭯﭰﭱﭲ
37:133 ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷ
37:134 እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡
ﭸﭹﭺﭻﭼ
37:135 (በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡
ﭽﭾﭿﮀ
37:136 ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡
ﮁﮂﮃﮄﮅ
37:137 እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡
ﮆﮇﮈﮉﮊ
37:138 በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን?
ﮋﮌﮍﮎﮏ
37:139 ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
ﮐﮑﮒﮓﮔﮕ
37:140 ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
ﮖﮗﮘﮙﮚ
37:141 ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡
ﮛﮜﮝﮞﮟ
37:142 እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡
ﮠﮡﮢﮣﮤﮥ
37:143 እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤
ﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬ
37:144 እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡
ﮭﮮﮯﮰﮱﯓ
37:145 እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡
ﯔﯕﯖﯗﯘﯙ
37:146 በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡
ﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠ
37:147 ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡
ﯡﯢﯣﯤﯥ
37:148 አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡
ﯦﯧﯨﯩﯪﯫ
37:149 (የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?»
ﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲ
37:150 ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?
ﯳﯴﯵﯶﯷﯸ
37:151 ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡-
ﯹﯺﯻﯼﯽ
37:152 «አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡
ﯾﯿﰀﰁﰂ
37:153 በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን?
ﭑﭒﭓﭔﭕ
37:154 ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
ﭖﭗﭘ
37:155 አትገነዘቡምን?
ﭙﭚﭛﭜﭝ
37:156 ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን?
ﭞﭟﭠﭡﭢﭣ
37:157 «እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡
ﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯ
37:158 በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡
ﭰﭱﭲﭳﭴ
37:159 አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
ﭵﭶﭷﭸﭹ
37:160 ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡
ﭺﭻﭼﭽ
37:161 እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤
ﭾﭿﮀﮁﮂ
37:162 በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡
ﮃﮄﮅﮆﮇﮈ
37:163 ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡
ﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏ
37:164 (ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡
ﮐﮑﮒﮓ
37:165 እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡
ﮔﮕﮖﮗ
37:166 እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡
ﮘﮙﮚﮛ
37:167 እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡-
ﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢ
37:168 «ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤
ﮣﮤﮥﮦﮧ
37:169 «የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡»
ﮨﮩﮪﮫﮬﮭ
37:170 ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
ﮮﮯﮰﮱﯓﯔ
37:171 (የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡
ﯕﯖﯗﯘ
37:172 እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
ﯙﯚﯛﯜﯝ
37:173 ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
ﯞﯟﯠﯡﯢ
37:174 ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡
ﯣﯤﯥﯦ
37:175 እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡
ﯧﯨﯩ
37:176 በቅጣታችንም ያቻኩላሉን?
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰ
37:177 በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
ﯱﯲﯳﯴﯵ
37:178 እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡
ﯶﯷﯸﯹ
37:179 ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡
ﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀ
37:180 የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
ﰁﰂﰃﰄ
37:181 በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤
ﰅﰆﰇﰈﰉ
37:182 ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers