አል-ኢምራን · 48/200
ትርጉም ፊደሎች — ሱረቱ አል-ኢምራን
وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ ۝٤٨
Wa yu`allimuhul Kitaaba wal Hikmata wat Tawraata wal Injeel
📖 በአማርኛ
ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል፡፡

🎧 ስሙ


📜 አንቀጽ 46-50 — ሱረቱ አል-ኢምራን

46وَيُكَلِّمُ النَّاسَ فِي الْمَهْدِ وَكَهْلًا وَمِنَ الصَّالِحِينَ
«በሕፃንነቱና በከፈኒሳነቱ ሰዎቹን ያነጋግራል፡፡ ከመልካሞቹም ነው» (አላት)፡፡
47قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡
48وَيُعَلِّمُهُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ
ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል፡፡
49وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ (ይላልም)፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡»
50وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَلِأُحِلَّ لَكُم بَعْضَ الَّذِي حُرِّمَ عَلَيْكُمْ ۚ وَجِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
«ከተውራትም ከእኔ በፊት ያለውን ያረጋገጥሁ ስኾን የዚያንም በእናንተ ላይ እርም የተደረገውን ከፊል ለእናንተ እፈቅድ ዘንድ (መጣኋችሁ) ከጌታችሁም በኾነ ታምር መጣሁዋችሁ፡፡ አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡»
አል-ኢምራንቁርአን ማውጫ
200አንቀጽ
MedinanRevelation
48አንቀጽ

ትርጉም — አል-ኢምራን 48

ሱረቱ አል-ኢምራን አንቀጽ 48 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል፡፡

ሱረቱ አንቀጽ 48/200 — ሱረቱ አል-ኢምራን آل عمران (Medinan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ሱረቱ አል-ኢምራን ስሙ, ሱረቱ አል-ኢምራን ትርጉም, ሱረቱ አል-ኢምራን mp3, ሱረቱ አል-ኢምራን pdf. አንቀጽ 46–50. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, September 8, 2026

Don't forget us in your sincere prayers