La sourate Al-Waqiah en Amharique
إِذَا وَقَعَتِ الْوَاقِعَةُ(1) መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡ |
لَيْسَ لِوَقْعَتِهَا كَاذِبَةٌ(2) ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡ |
خَافِضَةٌ رَّافِعَةٌ(3) ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡ |
إِذَا رُجَّتِ الْأَرْضُ رَجًّا(4) ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡ |
وَبُسَّتِ الْجِبَالُ بَسًّا(5) ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡ |
فَكَانَتْ هَبَاءً مُّنبَثًّا(6) የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ |
وَكُنتُمْ أَزْوَاجًا ثَلَاثَةً(7) ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡ |
فَأَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ مَا أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ(8) የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ |
وَأَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ مَا أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ(9) የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ |
وَالسَّابِقُونَ السَّابِقُونَ(10) (ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ |
أُولَٰئِكَ الْمُقَرَّبُونَ(11) እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡ |
فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ(12) በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡ |
ثُلَّةٌ مِّنَ الْأَوَّلِينَ(13) ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ |
وَقَلِيلٌ مِّنَ الْآخِرِينَ(14) ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡ |
عَلَىٰ سُرُرٍ مَّوْضُونَةٍ(15) በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡ |
مُّتَّكِئِينَ عَلَيْهَا مُتَقَابِلِينَ(16) በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡ |
يَطُوفُ عَلَيْهِمْ وِلْدَانٌ مُّخَلَّدُونَ(17) በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ |
بِأَكْوَابٍ وَأَبَارِيقَ وَكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍ(18) ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡ |
لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ(19) ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡ |
وَفَاكِهَةٍ مِّمَّا يَتَخَيَّرُونَ(20) ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡ |
وَلَحْمِ طَيْرٍ مِّمَّا يَشْتَهُونَ(21) ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡ |
وَحُورٌ عِينٌ(22) ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡ |
كَأَمْثَالِ اللُّؤْلُؤِ الْمَكْنُونِ(23) ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡ |
جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ(24) በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡ |
لَا يَسْمَعُونَ فِيهَا لَغْوًا وَلَا تَأْثِيمًا(25) በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡ |
إِلَّا قِيلًا سَلَامًا سَلَامًا(26) ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡ |
وَأَصْحَابُ الْيَمِينِ مَا أَصْحَابُ الْيَمِينِ(27) የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች! |
فِي سِدْرٍ مَّخْضُودٍ(28) በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡ |
وَطَلْحٍ مَّنضُودٍ(29) (ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡ |
وَظِلٍّ مَّمْدُودٍ(30) በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡ |
وَمَاءٍ مَّسْكُوبٍ(31) በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡ |
وَفَاكِهَةٍ كَثِيرَةٍ(32) ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡ |
لَّا مَقْطُوعَةٍ وَلَا مَمْنُوعَةٍ(33) የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡ |
وَفُرُشٍ مَّرْفُوعَةٍ(34) ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡ |
إِنَّا أَنشَأْنَاهُنَّ إِنشَاءً(35) እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡ |
فَجَعَلْنَاهُنَّ أَبْكَارًا(36) ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡ |
عُرُبًا أَتْرَابًا(37) ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡ |
لِّأَصْحَابِ الْيَمِينِ(38) ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡ |
ثُلَّةٌ مِّنَ الْأَوَّلِينَ(39) ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ |
وَثُلَّةٌ مِّنَ الْآخِرِينَ(40) ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ |
وَأَصْحَابُ الشِّمَالِ مَا أَصْحَابُ الشِّمَالِ(41) የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡ |
فِي سَمُومٍ وَحَمِيمٍ(42) በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡ |
وَظِلٍّ مِّن يَحْمُومٍ(43) ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡ |
لَّا بَارِدٍ وَلَا كَرِيمٍ(44) ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡ |
إِنَّهُمْ كَانُوا قَبْلَ ذَٰلِكَ مُتْرَفِينَ(45) እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡ |
وَكَانُوا يُصِرُّونَ عَلَى الْحِنثِ الْعَظِيمِ(46) በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡ |
وَكَانُوا يَقُولُونَ أَئِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَبْعُوثُونَ(47) ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን? |
أَوَآبَاؤُنَا الْأَوَّلُونَ(48) «የፊተኞቹ አባቶቻችንም?» |
قُلْ إِنَّ الْأَوَّلِينَ وَالْآخِرِينَ(49) በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡ |
لَمَجْمُوعُونَ إِلَىٰ مِيقَاتِ يَوْمٍ مَّعْلُومٍ(50) «በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡ |
ثُمَّ إِنَّكُمْ أَيُّهَا الضَّالُّونَ الْمُكَذِّبُونَ(51) «ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ! |
لَآكِلُونَ مِن شَجَرٍ مِّن زَقُّومٍ(52) « ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡ |
فَمَالِئُونَ مِنْهَا الْبُطُونَ(53) «ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡ |
فَشَارِبُونَ عَلَيْهِ مِنَ الْحَمِيمِ(54) «በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡ |
فَشَارِبُونَ شُرْبَ الْهِيمِ(55) «የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡» |
هَٰذَا نُزُلُهُمْ يَوْمَ الدِّينِ(56) ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡ |
نَحْنُ خَلَقْنَاكُمْ فَلَوْلَا تُصَدِّقُونَ(57) እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን? |
أَفَرَأَيْتُم مَّا تُمْنُونَ(58) (በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን? |
أَأَنتُمْ تَخْلُقُونَهُ أَمْ نَحْنُ الْخَالِقُونَ(59) እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን? |
نَحْنُ قَدَّرْنَا بَيْنَكُمُ الْمَوْتَ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ(60) እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ |
عَلَىٰ أَن نُّبَدِّلَ أَمْثَالَكُمْ وَنُنشِئَكُمْ فِي مَا لَا تَعْلَمُونَ(61) ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡ |
وَلَقَدْ عَلِمْتُمُ النَّشْأَةَ الْأُولَىٰ فَلَوْلَا تَذَكَّرُونَ(62) የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን? |
أَفَرَأَيْتُم مَّا تَحْرُثُونَ(63) የምትዘሩትንም አያችሁን? |
أَأَنتُمْ تَزْرَعُونَهُ أَمْ نَحْنُ الزَّارِعُونَ(64) እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን? |
لَوْ نَشَاءُ لَجَعَلْنَاهُ حُطَامًا فَظَلْتُمْ تَفَكَّهُونَ(65) ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡ |
إِنَّا لَمُغْرَمُونَ(66) «እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡ |
بَلْ نَحْنُ مَحْرُومُونَ(67) «በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡ |
أَفَرَأَيْتُمُ الْمَاءَ الَّذِي تَشْرَبُونَ(68) ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን? |
أَأَنتُمْ أَنزَلْتُمُوهُ مِنَ الْمُزْنِ أَمْ نَحْنُ الْمُنزِلُونَ(69) እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን? |
لَوْ نَشَاءُ جَعَلْنَاهُ أُجَاجًا فَلَوْلَا تَشْكُرُونَ(70) ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን? |
أَفَرَأَيْتُمُ النَّارَ الَّتِي تُورُونَ(71) ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን? |
أَأَنتُمْ أَنشَأْتُمْ شَجَرَتَهَا أَمْ نَحْنُ الْمُنشِئُونَ(72) እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን? |
نَحْنُ جَعَلْنَاهَا تَذْكِرَةً وَمَتَاعًا لِّلْمُقْوِينَ(73) እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡ |
فَسَبِّحْ بِاسْمِ رَبِّكَ الْعَظِيمِ(74) የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡ |
۞ فَلَا أُقْسِمُ بِمَوَاقِعِ النُّجُومِ(75) በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡ |
وَإِنَّهُ لَقَسَمٌ لَّوْ تَعْلَمُونَ عَظِيمٌ(76) እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡ |
إِنَّهُ لَقُرْآنٌ كَرِيمٌ(77) እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ |
فِي كِتَابٍ مَّكْنُونٍ(78) በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ |
لَّا يَمَسُّهُ إِلَّا الْمُطَهَّرُونَ(79) የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡ |
تَنزِيلٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ(80) ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ |
أَفَبِهَٰذَا الْحَدِيثِ أَنتُم مُّدْهِنُونَ(81) በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን? |
وَتَجْعَلُونَ رِزْقَكُمْ أَنَّكُمْ تُكَذِّبُونَ(82) ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን? |
فَلَوْلَا إِذَا بَلَغَتِ الْحُلْقُومَ(83) (ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡ |
وَأَنتُمْ حِينَئِذٍ تَنظُرُونَ(84) እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡ |
وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنكُمْ وَلَٰكِن لَّا تُبْصِرُونَ(85) እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡ |
فَلَوْلَا إِن كُنتُمْ غَيْرَ مَدِينِينَ(86) የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡ |
تَرْجِعُونَهَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ(87) እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡ |
فَأَمَّا إِن كَانَ مِنَ الْمُقَرَّبِينَ(88) (ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡ |
فَرَوْحٌ وَرَيْحَانٌ وَجَنَّتُ نَعِيمٍ(89) (ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡ |
وَأَمَّا إِن كَانَ مِنْ أَصْحَابِ الْيَمِينِ(90) ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡ |
فَسَلَامٌ لَّكَ مِنْ أَصْحَابِ الْيَمِينِ(91) ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡ |
وَأَمَّا إِن كَانَ مِنَ الْمُكَذِّبِينَ الضَّالِّينَ(92) ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡ |
فَنُزُلٌ مِّنْ حَمِيمٍ(93) ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡ |
وَتَصْلِيَةُ جَحِيمٍ(94) በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡ |
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ حَقُّ الْيَقِينِ(95) ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡ |
فَسَبِّحْ بِاسْمِ رَبِّكَ الْعَظِيمِ(96) የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Waqiah : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Waqiah complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide