Перевод суры Аль-Муминун на амхарский язык

  1. Сура mp3
  2. Другие суры
  3. амхарский
Священный Коран | Перевод Корана | Язык амхарский | Сура Аль-Муминун | المؤمنون - получите точный и надежный амхарский текст сейчас - Количество аятов: 118 - Номер суры в мушафе: 23 - Значение названия суры на русском языке: The Believers.

قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ(1)

 ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡

الَّذِينَ هُمْ فِي صَلَاتِهِمْ خَاشِعُونَ(2)

 እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡

وَالَّذِينَ هُمْ عَنِ اللَّغْوِ مُعْرِضُونَ(3)

 እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፡፡

وَالَّذِينَ هُمْ لِلزَّكَاةِ فَاعِلُونَ(4)

 እነዚያም እነርሱ ዘካን ሰጭዎች፡፡

وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ(5)

 እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡

إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ(6)

 በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡

فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ(7)

 ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፡፡

وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ(8)

 እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፡፡

وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَوَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ(9)

 እነዚያም እነሱ በስግደቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁ የኸኑት (አገኙ)፡፡

أُولَٰئِكَ هُمُ الْوَارِثُونَ(10)

 እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው፡፡

الَّذِينَ يَرِثُونَ الْفِرْدَوْسَ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ(11)

 እነዚያ ፊርደውስን (ላዕላይ ገነትን)፤ የሚወርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡

وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن سُلَالَةٍ مِّن طِينٍ(12)

 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፡፡

ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ(13)

 ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡

ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ(14)

 ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡

ثُمَّ إِنَّكُم بَعْدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ(15)

 ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ፡፡

ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ تُبْعَثُونَ(16)

 ከዚያም እናንተ በትንሣኤ ቀን ትቀሰቀሳላችሁ፡፡

وَلَقَدْ خَلَقْنَا فَوْقَكُمْ سَبْعَ طَرَائِقَ وَمَا كُنَّا عَنِ الْخَلْقِ غَافِلِينَ(17)

 በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን፡፡ ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም፡፡

وَأَنزَلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً بِقَدَرٍ فَأَسْكَنَّاهُ فِي الْأَرْضِ ۖ وَإِنَّا عَلَىٰ ذَهَابٍ بِهِ لَقَادِرُونَ(18)

 ከሰማይም ውሃን በልክ አወረድን፡፡ በምድርም ውስጥ አስቀመጥነው፡፡ እኛም እርሱን በማስወገድ ላይ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡

فَأَنشَأْنَا لَكُم بِهِ جَنَّاتٍ مِّن نَّخِيلٍ وَأَعْنَابٍ لَّكُمْ فِيهَا فَوَاكِهُ كَثِيرَةٌ وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ(19)

 በእርሱም ከዘምባባዎችና ከወይኖች የኾኑን አትክልቶች ለእናንተ አስገኘንላችሁ፡፡ በውስጧ ለእናንተ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁ፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡

وَشَجَرَةً تَخْرُجُ مِن طُورِ سَيْنَاءَ تَنبُتُ بِالدُّهْنِ وَصِبْغٍ لِّلْآكِلِينَ(20)

 ከሲና ተራራም የምትወጣን ዛፍ በቅባትና ለበይዎችም መባያ በሚኾን (ዘይት) ተቀላቅላ የምትበቅልን (አስገኘንላችሁ)፡፡

وَإِنَّ لَكُمْ فِي الْأَنْعَامِ لَعِبْرَةً ۖ نُّسْقِيكُم مِّمَّا فِي بُطُونِهَا وَلَكُمْ فِيهَا مَنَافِعُ كَثِيرَةٌ وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ(21)

 ለእናንተም በግመል፣ በከብት፣ በፍየልና በበግ መገምገሚያ አልላችሁ፡፡ በሆዶችዋ ውስጥ ካለው (ወተት) እናጠጣችኋለን፡፡ ለእናንተም በእርሷ ብዙ ጥቅሞች አሏችሁ፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡

وَعَلَيْهَا وَعَلَى الْفُلْكِ تُحْمَلُونَ(22)

 በእርሷም ላይ በመርከብም ላይ ትጫናላችሁ፡፡

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ أَفَلَا تَتَّقُونَ(23)

 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ አትጠነቀቁምን» አላቸው፡፡

فَقَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَوْمِهِ مَا هَٰذَا إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُرِيدُ أَن يَتَفَضَّلَ عَلَيْكُمْ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَأَنزَلَ مَلَائِكَةً مَّا سَمِعْنَا بِهَٰذَا فِي آبَائِنَا الْأَوَّلِينَ(24)

 ከሕዝቦቹም እነዚያ ታላላቆቹ ሰዎች አሉ «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ በእናንተ ላይ መብለጥን ይፈልጋል፡፡ አላህም በሻ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር፡፡ ይህንንም (የሚለውን) በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አልሰማንም፡፡

إِنْ هُوَ إِلَّا رَجُلٌ بِهِ جِنَّةٌ فَتَرَبَّصُوا بِهِ حَتَّىٰ حِينٍ(25)

 «እርሱ በእርሱ ዕብደት ያለበት ሰው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ በእርሱም እስከ ጊዜ (ሞቱ) ድረስ ተጠባበቁ» (አሉ)፡፡

قَالَ رَبِّ انصُرْنِي بِمَا كَذَّبُونِ(26)

 (ኑሕም) «ጌታዬ ሆይ! ባስተባበሉኝ ምክንያት እርዳኝ» አለ፡፡

فَأَوْحَيْنَا إِلَيْهِ أَنِ اصْنَعِ الْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا فَإِذَا جَاءَ أَمْرُنَا وَفَارَ التَّنُّورُ ۙ فَاسْلُكْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ الْقَوْلُ مِنْهُمْ ۖ وَلَا تُخَاطِبْنِي فِي الَّذِينَ ظَلَمُوا ۖ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ(27)

 ወደርሱም (እንዲህ ስንል) ላክን «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችንም ታንኳን ሥራ በመጣና እቶኑ በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ሁለት ዓይነቶችን ቤተሰቦችህንም ከነሱ (ጠፊ በመኾን) ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር፤ አግባ፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታነጋግረኝ፡፡ እነሱ ተሰጣሚዎች ነቸውና፡፡

فَإِذَا اسْتَوَيْتَ أَنتَ وَمَن مَّعَكَ عَلَى الْفُلْكِ فَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي نَجَّانَا مِنَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ(28)

 አንተም አብረውህ ካሉት ጋር በታንኳይቱ ላይ በተደላደልክ ጊዜ «ምስጋና ለዚያ ከበደለኞች ሕዝቦች ላዳነን አላህ ይገባው» በል፡፡

وَقُل رَّبِّ أَنزِلْنِي مُنزَلًا مُّبَارَكًا وَأَنتَ خَيْرُ الْمُنزِلِينَ(29)

 በልም «ጌታዬ ሆይ! ብሩክ የኾነን ማውረድ አውርደኝ፡፡ አንተም ከአውራጆች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ وَإِن كُنَّا لَمُبْتَلِينَ(30)

 በዚህ ውስጥ (ለከሃሊነታችን) ምልከቶች አልሉበት፡፡ እነሆ! (የኑሕን ሰዎች) በእርግጥም ፈትታኞች ነበርን፡፡

ثُمَّ أَنشَأْنَا مِن بَعْدِهِمْ قَرْنًا آخَرِينَ(31)

 ከዚያም ከኋላቸው ሌሎችን የክፍለ ዘመን ሕዝቦች አስገኘን፡፡

فَأَرْسَلْنَا فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ أَفَلَا تَتَّقُونَ(32)

 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን በማለት ላክን፡፡

وَقَالَ الْمَلَأُ مِن قَوْمِهِ الَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِلِقَاءِ الْآخِرَةِ وَأَتْرَفْنَاهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا مَا هَٰذَا إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يَأْكُلُ مِمَّا تَأْكُلُونَ مِنْهُ وَيَشْرَبُ مِمَّا تَشْرَبُونَ(33)

 ከሕዝቦቹም እነዚያ የካዱት በመጨረሻይቱም ቀን መገናኘት ያስተባበሉት በቅርቢቱም ሕይወት ያቀማጠልናቸው ታላላቅ ሰዎች «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ከርሱ ከምትበሉት ምግብ ይበላል፡፡ ከምትጠጡትም ውሃ ይጠጣል» አሉ፡፡

وَلَئِنْ أَطَعْتُم بَشَرًا مِّثْلَكُمْ إِنَّكُمْ إِذًا لَّخَاسِرُونَ(34)

 «ብጤያችሁም የኾነን ሰው ብትታዘዙ እናንተ ያን ጊዜ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናቸሁ» (አሉ)፡፡

أَيَعِدُكُمْ أَنَّكُمْ إِذَا مِتُّمْ وَكُنتُمْ تُرَابًا وَعِظَامًا أَنَّكُم مُّخْرَجُونَ(35)

 «እናንተ በሞታችሁና ዐፈርና አጥንቶችም በኾናችሁ ጊዜ እናንተ (ከመቃብር) ትወጣላችሁ በማለት ያስፈራራችኋልን

۞ هَيْهَاتَ هَيْهَاتَ لِمَا تُوعَدُونَ(36)

 «ያ የምትስፈራሩበት ነገር ራቀ፤ በጣም ራቀ፡፡

إِنْ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا الدُّنْيَا نَمُوتُ وَنَحْيَا وَمَا نَحْنُ بِمَبْعُوثِينَ(37)

 «እርሷ (ሕይወት) ቅርቢቱ ሕይወታችን እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ እንሞታለን፤ (ልጆቻችን ስለሚተኩ) ሕያውም እንኾናለን፡፡ እኛም ተቀስቃሾች አይደለንም፡፡

إِنْ هُوَ إِلَّا رَجُلٌ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا وَمَا نَحْنُ لَهُ بِمُؤْمِنِينَ(38)

 «እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እኛም ለእርሱ አማኞች አይደለንም» (አሉ)፡፡

قَالَ رَبِّ انصُرْنِي بِمَا كَذَّبُونِ(39)

 (መልክተኛውም) «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ እርዳኝ» አለ፡፡

قَالَ عَمَّا قَلِيلٍ لَّيُصْبِحُنَّ نَادِمِينَ(40)

 (አላህም) «ከጥቂት ጊዜ በኋላ (በጥፋታቸው) በእርግጥ ተጸጻቾች ይኾናሉ» አለው፡፡

فَأَخَذَتْهُمُ الصَّيْحَةُ بِالْحَقِّ فَجَعَلْنَاهُمْ غُثَاءً ۚ فَبُعْدًا لِّلْقَوْمِ الظَّالِمِينَ(41)

 ወዲያውም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፡፡ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም አደረግናቸው፡፡ ለበደለኞች ሕዝቦችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡

ثُمَّ أَنشَأْنَا مِن بَعْدِهِمْ قُرُونًا آخَرِينَ(42)

 ከዚያም ከእነሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ሕዝቦች አስገኘን፡፡

مَا تَسْبِقُ مِنْ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسْتَأْخِرُونَ(43)

 ማንኛይቱም ሕዝብ ጊዜያዋን አትቀድምም፤ አይቅቆዩምም፡፡

ثُمَّ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا تَتْرَىٰ ۖ كُلَّ مَا جَاءَ أُمَّةً رَّسُولُهَا كَذَّبُوهُ ۚ فَأَتْبَعْنَا بَعْضَهُم بَعْضًا وَجَعَلْنَاهُمْ أَحَادِيثَ ۚ فَبُعْدًا لِّقَوْمٍ لَّا يُؤْمِنُونَ(44)

 ከዚያም መልክተኞቻችንን የሚከታተሉ ኾነው ላክን፡፡ ማንኛይቱንም ሕዝብ መልክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት፡፡ ከፊላቸውንም በከፊሉ (በጥፋት) አስከታተለን፡፡ ወሬዎችም አደረግናቸው፡፡ ለማያምኑም ሕዝቦች (ከእዝነታችን) መራቅ ተገባቸው፡፡

ثُمَّ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَارُونَ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ(45)

 ከዚያም ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላክን፡፡

إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا عَالِينَ(46)

 ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ (ላክናቸው)፡፡ ኮሩም፡፡ የተንበጣረሩ ሕዝቦችም ነበሩ፡፡

فَقَالُوا أَنُؤْمِنُ لِبَشَرَيْنِ مِثْلِنَا وَقَوْمُهُمَا لَنَا عَابِدُونَ(47)

 «ብጤያችንም ለኾኑ ሁለት ሰዎች ሕዝቦቻቸው ለእኛ ተገዢዎች ኾነው ሳሉ እናምናለን» አሉ፡፡

فَكَذَّبُوهُمَا فَكَانُوا مِنَ الْمُهْلَكِينَ(48)

 አስተባበሉዋቸውም፡፡ ከጠፊዎቹም ኾኑ፡፡

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ لَعَلَّهُمْ يَهْتَدُونَ(49)

 ሙሳንም (ነገዶቹ) ይምመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡

وَجَعَلْنَا ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ آيَةً وَآوَيْنَاهُمَا إِلَىٰ رَبْوَةٍ ذَاتِ قَرَارٍ وَمَعِينٍ(50)

 የመርየምን ልጅና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው፡፡ የመደላደልና የምንጭ ባለቤት ወደ ኾነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው፡፡

يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ(51)

 እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ፡፡

وَإِنَّ هَٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاتَّقُونِ(52)

 ይህችም (በአንድ አምላክ የማመን ሕግጋት) አንድ መንገድ ስትኾን ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ፡፡

فَتَقَطَّعُوا أَمْرَهُم بَيْنَهُمْ زُبُرًا ۖ كُلُّ حِزْبٍ بِمَا لَدَيْهِمْ فَرِحُونَ(53)

 (ከዚያ ተከታዮቻቸው) የሃይማኖት ነገራቸውንም በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው ቆራረጡ፡፡ ሕዝብ ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው፡፡

فَذَرْهُمْ فِي غَمْرَتِهِمْ حَتَّىٰ حِينٍ(54)

 እስከ ጊዜያቸውም ድረስ በጥምመታቸው ውስጥ ተዋቸው፡፡

أَيَحْسَبُونَ أَنَّمَا نُمِدُّهُم بِهِ مِن مَّالٍ وَبَنِينَ(55)

 ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን

نُسَارِعُ لَهُمْ فِي الْخَيْرَاتِ ۚ بَل لَّا يَشْعُرُونَ(56)

 በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው መኾንን (ያስባሉን) አይደለም፤ (ለማዘንጋት መኾኑን) አያውቁም፡፡

إِنَّ الَّذِينَ هُم مِّنْ خَشْيَةِ رَبِّهِم مُّشْفِقُونَ(57)

 እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የኾኑት፡፡

وَالَّذِينَ هُم بِآيَاتِ رَبِّهِمْ يُؤْمِنُونَ(58)

 እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራቶች ከሚያምኑት፡፡

وَالَّذِينَ هُم بِرَبِّهِمْ لَا يُشْرِكُونَ(59)

 እነዚያም እነርሱ በጌታቸው (ጣዖትን) የማያጋሩት፡፡

وَالَّذِينَ يُؤْتُونَ مَا آتَوا وَّقُلُوبُهُمْ وَجِلَةٌ أَنَّهُمْ إِلَىٰ رَبِّهِمْ رَاجِعُونَ(60)

 እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡

أُولَٰئِكَ يُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَهُمْ لَهَا سَابِقُونَ(61)

 እነዚያ በመልካም ሥራዎች ይጣደፋሉ፡፡ እነሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡

وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۖ وَلَدَيْنَا كِتَابٌ يَنطِقُ بِالْحَقِّ ۚ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ(62)

 ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም፡፡ እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አልለ፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡

بَلْ قُلُوبُهُمْ فِي غَمْرَةٍ مِّنْ هَٰذَا وَلَهُمْ أَعْمَالٌ مِّن دُونِ ذَٰلِكَ هُمْ لَهَا عَامِلُونَ(63)

 በእውነቱ (ከሓዲዎች) ልቦቻቸው ከዚያ (መጽሐፍ) በዝንጋቴ ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነሱም ከዚህ ሌላ እነሱ ለርሷ ሠሪዎችዋ የኾኑ (መጥፎ) ሥራዎች አሏቸው፡፡

حَتَّىٰ إِذَا أَخَذْنَا مُتْرَفِيهِم بِالْعَذَابِ إِذَا هُمْ يَجْأَرُونَ(64)

 ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ፡፡

لَا تَجْأَرُوا الْيَوْمَ ۖ إِنَّكُم مِّنَّا لَا تُنصَرُونَ(65)

 ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱም፡፡

قَدْ كَانَتْ آيَاتِي تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَكُنتُمْ عَلَىٰ أَعْقَابِكُمْ تَنكِصُونَ(66)

 አንቀጾቹ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር፡፡ በተረከዞቻችሁም ላይ ወደ ኋላችሁ ትመለሱ ነበራችሁ፡፡

مُسْتَكْبِرِينَ بِهِ سَامِرًا تَهْجُرُونَ(67)

 በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ኾናችሁ (ትመለሱ ነበራችሁ ይባላሉ)፡፡

أَفَلَمْ يَدَّبَّرُوا الْقَوْلَ أَمْ جَاءَهُم مَّا لَمْ يَأْتِ آبَاءَهُمُ الْأَوَّلِينَ(68)

 (የቁርኣንን) ንግግሩንም አያስተነትኑምን ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን

أَمْ لَمْ يَعْرِفُوا رَسُولَهُمْ فَهُمْ لَهُ مُنكِرُونَ(69)

 ወይስ መልክተኛቸውን አላወቁምን ስለዚህ እነርሱ ለእርሱ ከሓዲዎች ናቸውን

أَمْ يَقُولُونَ بِهِ جِنَّةٌ ۚ بَلْ جَاءَهُم بِالْحَقِّ وَأَكْثَرُهُمْ لِلْحَقِّ كَارِهُونَ(70)

 ወይስ በእርሱ ዕብደት አለበት ይላሉን አይደለም፡፡ እውነትን ይዞ መጣላቸው፡፡ አብዛኞቻቸውም እውነትን ጠይዎች ናቸው፡፡

وَلَوِ اتَّبَعَ الْحَقُّ أَهْوَاءَهُمْ لَفَسَدَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ وَمَن فِيهِنَّ ۚ بَلْ أَتَيْنَاهُم بِذِكْرِهِمْ فَهُمْ عَن ذِكْرِهِم مُّعْرِضُونَ(71)

 አላህም ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ በእርግጥ በተበላሸ ነበር፡፡ ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን ቁርኣን አመጣንላቸው፡፡ እነርሱም ከክብራቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡

أَمْ تَسْأَلُهُمْ خَرْجًا فَخَرَاجُ رَبِّكَ خَيْرٌ ۖ وَهُوَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ(72)

 ወይስ ግብርን ትጠይቃቸዋለህን የጌታህም ችሮታ በላጭ ነው፡፡ እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው፡፡

وَإِنَّكَ لَتَدْعُوهُمْ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ(73)

 አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ፡፡

وَإِنَّ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ عَنِ الصِّرَاطِ لَنَاكِبُونَ(74)

 እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው፡፡

۞ وَلَوْ رَحِمْنَاهُمْ وَكَشَفْنَا مَا بِهِم مِّن ضُرٍّ لَّلَجُّوا فِي طُغْيَانِهِمْ يَعْمَهُونَ(75)

 ባዘንንላቸውና ከጉዳትም በእነርሱ ያለውን ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ኾነው ይዘወትሩ ነበር፡፡

وَلَقَدْ أَخَذْنَاهُم بِالْعَذَابِ فَمَا اسْتَكَانُوا لِرَبِّهِمْ وَمَا يَتَضَرَّعُونَ(76)

 በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው፡፡ ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም፡፡ አይዋደቁምም፡፡

حَتَّىٰ إِذَا فَتَحْنَا عَلَيْهِم بَابًا ذَا عَذَابٍ شَدِيدٍ إِذَا هُمْ فِيهِ مُبْلِسُونَ(77)

 በእነሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የኾነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው፡፡

وَهُوَ الَّذِي أَنشَأَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۚ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ(78)

 እርሱም ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡

وَهُوَ الَّذِي ذَرَأَكُمْ فِي الْأَرْضِ وَإِلَيْهِ تُحْشَرُونَ(79)

 እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው፡፡ ወደርሱም ትሰበሰባላችሁ፡፡

وَهُوَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ وَلَهُ اخْتِلَافُ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ(80)

 እርሱም ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው፡፡ አታውቁምን

بَلْ قَالُوا مِثْلَ مَا قَالَ الْأَوَّلُونَ(81)

 ይልቁንም (የመካ ከሓዲዎች) የፊተኞቹ ሕዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ፡፡

قَالُوا أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَبْعُوثُونَ(82)

 «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶች በኾን ጊዜ እኛ ተቀስቃሾች ነን» አሉ፡፡

لَقَدْ وُعِدْنَا نَحْنُ وَآبَاؤُنَا هَٰذَا مِن قَبْلُ إِنْ هَٰذَا إِلَّا أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ(83)

 «ይህንን እኛም ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፡፡ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» (አሉ)፡፡

قُل لِّمَنِ الْأَرْضُ وَمَن فِيهَا إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ(84)

 «ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)» በላቸው፡፡

سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ(85)

 «በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን» በላቸው፡፡

قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ(86)

 «የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡

سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ(87)

 «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡

قُلْ مَن بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ(88)

 «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡

سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ فَأَنَّىٰ تُسْحَرُونَ(89)

 «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ» በላቸው፡፡

بَلْ أَتَيْنَاهُم بِالْحَقِّ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ(90)

 ይልቁንም እውነትን አመጣንላቸው፡፡ እነርሱም (በመካዳቸው) ውሸታሞች ናቸው፡፡

مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَٰهٍ ۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ(91)

 አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላ አምላክ በነበረ) አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡

عَالِمِ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ(92)

 ሩቁንና ቅርቡንም ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ (በእርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ፡፡

قُل رَّبِّ إِمَّا تُرِيَنِّي مَا يُوعَدُونَ(93)

 (ሙሐመድ ሆይ!) በል «ጌታዬ ሆይ! የሚያስፈራሩበትን (ቅጣት) ብታሳየኝ፡፡

رَبِّ فَلَا تَجْعَلْنِي فِي الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ(94)

 «ጌታዬ ሆይ! በበደለኞች ሕዝቦች ውስጥ አታድርገኝ፡፡»

وَإِنَّا عَلَىٰ أَن نُّرِيَكَ مَا نَعِدُهُمْ لَقَادِرُونَ(95)

 እኛም የምናስፈራራቸውን ነገር ልናሳይህ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡

ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ السَّيِّئَةَ ۚ نَحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَصِفُونَ(96)

 በዚያች እርስዋ መልካም በኾነችው (ጠባይ) መጥፎይቱን ነገር ገፍትር፡፡ እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂዎች ነን፡፡

وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ(97)

 በልም «ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ፡፡

وَأَعُوذُ بِكَ رَبِّ أَن يَحْضُرُونِ(98)

 «ባንተም ጌታዬ ሆይ! (በነገሮቼ) ወደእኔ ከመጣዳቸው እጠበቃለሁ፡፡»

حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ(99)

 አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡

لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا ۖ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ(100)

 «በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» (ይህን ከማለት) ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አልለ፡፡

فَإِذَا نُفِخَ فِي الصُّورِ فَلَا أَنسَابَ بَيْنَهُمْ يَوْمَئِذٍ وَلَا يَتَسَاءَلُونَ(101)

 በቀንዱም በተነፋ ጊዜ በዚያ ቀን በመካከላቸው ዝምድና የለም፡፡ አይጠያየቁምም፡፡

فَمَن ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ(102)

 ሚዛኖቹም የከበዱለት ሰው እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡

وَمَنْ خَفَّتْ مَوَازِينُهُ فَأُولَٰئِكَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنفُسَهُمْ فِي جَهَنَّمَ خَالِدُونَ(103)

 ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰው እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡ በገሀነም ውስጥ ዘመውታሪዎች ናቸው፡፡

تَلْفَحُ وُجُوهَهُمُ النَّارُ وَهُمْ فِيهَا كَالِحُونَ(104)

 ፊቶቻቸውን እሳት ትገርፉቸዋለች፡፡ እነርሱም በእርሷ ውስጥ ከንፈሮቻቸው የተኮማተሩ ናቸው፡፡

أَلَمْ تَكُنْ آيَاتِي تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَكُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ(105)

 «አንቀጾቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን» (ይባላሉ)፡፡

قَالُوا رَبَّنَا غَلَبَتْ عَلَيْنَا شِقْوَتُنَا وَكُنَّا قَوْمًا ضَالِّينَ(106)

 ይላሉ «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችን፡፡ ጠማማዎችም ሕዝቦች ነበርን፡፡

رَبَّنَا أَخْرِجْنَا مِنْهَا فَإِنْ عُدْنَا فَإِنَّا ظَالِمُونَ(107)

 «ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣን፡፡ (ወደ ክህደት) ብንመለስም እኛ በደዮች ነን፡፡»

قَالَ اخْسَئُوا فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ(108)

 (አላህም) «ወራዶች ኾናችሁ በውስጥዋ እርጉ፡፡ አታናግሩኝም» ይላቸዋል፡፡

إِنَّهُ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْ عِبَادِي يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا وَأَنتَ خَيْرُ الرَّاحِمِينَ(109)

 እነሆ ከባሮቼ «ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን፡፡ እዘንልንም አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» የሚሉ ክፍሎች ነበሩ፡፡

فَاتَّخَذْتُمُوهُمْ سِخْرِيًّا حَتَّىٰ أَنسَوْكُمْ ذِكْرِي وَكُنتُم مِّنْهُمْ تَضْحَكُونَ(110)

 እኔንም ማውሳትን እስካስረሷችሁ ድረስም ማላገጫ አድርጋችሁ ያዛችኋቸው፡፡ በእነርሱም የምትስቁ ነበራችሁ፡፡

إِنِّي جَزَيْتُهُمُ الْيَوْمَ بِمَا صَبَرُوا أَنَّهُمْ هُمُ الْفَائِزُونَ(111)

 እኔ ዛሬ በትዕግስታቸው ምክንያት እነሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙት እነርሱ ብቻ በመኾን መነዳኋቸው፤ (ይላቸዋል)፡፡

قَالَ كَمْ لَبِثْتُمْ فِي الْأَرْضِ عَدَدَ سِنِينَ(112)

 «በምድር ውስጥ ከዓመታት ቁጥር ስንትን ቆያችሁ» ይላቸዋል፡፡

قَالُوا لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ فَاسْأَلِ الْعَادِّينَ(113)

 «አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን፡፡ ቆጣሪዎቹንም ጠይቅ» ይላሉ፡፡

قَالَ إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا ۖ لَّوْ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ(114)

 «እናንተ (የቆያችሁትን መጠን) የምታውቁ ብትኾኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ በምትቆዩት አንፃር) ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም» ይላቸዋል፡፡

أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ(115)

 «የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)

فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ ۖ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ(116)

 የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡

وَمَن يَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ لَا بُرْهَانَ لَهُ بِهِ فَإِنَّمَا حِسَابُهُ عِندَ رَبِّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الْكَافِرُونَ(117)

 ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡

وَقُل رَّبِّ اغْفِرْ وَارْحَمْ وَأَنتَ خَيْرُ الرَّاحِمِينَ(118)

 በልም «ጌታዬ ሆይ ማር፤ እዘንም፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»


Больше сур в амхарский:


Аль-Бакара Аль-'Имран Ан-Ниса'
Аль-Маида Юсуф Ибрахим
Аль-Хиджр Аль-Кахф Марьям
Аль-Хадж Аль-Касас Аль-'Анкабут
Ас-Саджда Я-Син Ад-Духан
Аль-Фатх Аль-Худжурат Каф
Ан-Наджм Ар-Рахман Аль-Ваки'а
Аль-Хашр Аль-Мульк Аль-Хакка
Аль-Иншикак Аль-А'ла Аль-Гашия

Скачать суру Al-Muminun с голосом самых известных рекитаторов Корана:

Сура Al-Muminun mp3: выберите рекитатора, чтобы прослушать и скачать главу Al-Muminun полностью в высоком качестве
surah Al-Muminun Ahmed El Agamy
Ahmed Al Ajmy
surah Al-Muminun Bandar Balila
Bandar Balila
surah Al-Muminun Khalid Al Jalil
Khalid Al Jalil
surah Al-Muminun Saad Al Ghamdi
Saad Al Ghamdi
surah Al-Muminun Saud Al Shuraim
Saud Al Shuraim
surah Al-Muminun Abdul Basit Abdul Samad
Abdul Basit
surah Al-Muminun Abdul Rashid Sufi
Abdul Rashid Sufi
surah Al-Muminun Abdullah Basfar
Abdullah Basfar
surah Al-Muminun Abdullah Awwad Al Juhani
Abdullah Al Juhani
surah Al-Muminun Fares Abbad
Fares Abbad
surah Al-Muminun Maher Al Muaiqly
Maher Al Muaiqly
surah Al-Muminun Muhammad Siddiq Al Minshawi
Al Minshawi
surah Al-Muminun Al Hosary
Al Hosary
surah Al-Muminun Al-afasi
Mishari Al-afasi
surah Al-Muminun Yasser Al Dosari
Yasser Al Dosari


Wednesday, January 22, 2025

Помолитесь за нас хорошей молитвой